1 በዚህ ጊዜ እስራኤላውያንን ከመፍራት የተነሣ፣ ኢያሪኮ ፈጽማ ተዘግታ ነበር፤ ወደ ውጭ የሚወጣም ሆነ ወደ ውስጥ የሚገባ አልነበረም።
2 እግዚአብሔርም ኢያሱን እንዲህ አለው፤ “እነሆ፤ ኢያሪኮን ከንጉሥዋና ከተዋጊዎቿ ጋር አሳልፌ በእጅህ ሰጥቻለሁ።
3 ከተማዪቱን ከተዋጊዎቻችሁ ጋር አንድ ጊዜ ዙሩ፤ ይህንም ስድስት ቀን አድርጉ።
4 ሰባት ካህናት፣ ሰባት ቀንደ መለከት ተሸክመው በታቦቱ ፊት ይውጡ፤ በሰባተኛውም ቀን ካህናቱ መለከት እየነፉ ከተማይቱን ሰባት ጊዜ ይዙሩ።