ኢያሱ 9:13-19 NASV

13 እነዚህ የወይን ጠጅ አቍማዳዎቻችን ያን ጊዜ ስንሞላቸው አዲስ ነበሩ፤ አሁን ግን እንዴት እንደተ ቀዳደዱ ተመልከቱ፤ ልብሳችንና ጫማችንም ብዙ መንገድ በመጓዛችን አልቀዋል።”

14 የእስራኤልም ሰዎች ከስንቃችው ላይ ጥቂት ወሰዱ፤ ስለ ጒዳዩ ግን እግዚአብሔርን አልጠየቁም ነበር።

15 ኢያሱም በሰላም ለመኖር የሚያስችላቸውን ቃል ኪዳን ከእነርሱ ጋር አደረገ፤ የጉባኤውም መሪዎች ይህንኑ በመሓላ አጸኑላቸው።

16 እስራኤላውያን ከገባዖን ሰዎች ጋር ቃል ኪዳኑን ካደረጉ ከሦስት ቀን በኋላ፣ ሰዎቹ እዚያው አጠገባቸው የሚኖሩ ጎረቤቶቻቸው መሆናቸውን ሰሙ።

17 ስለዚህ እስራኤላውያን ተጒዘው በሦስተኛው ቀን ገባዖን፣ ከፊራ፣ ብኤሮትና ቂርያትይዓይሪም ወደተባሉት የገባዖን ሰዎች ወደሚኖሩባቸው ከተሞች መጡ።

18 ሆኖም እስራኤላውያን አልወጓቸውም፤ የጉባዔው መሪዎች በእስራኤል አምላክ በእግዚአብሔር ስም ምለውላቸው ነበርና።ማኅበሩም ሁሉ በመሪዎቹ ላይ አጒረመረሙ፤

19 ነገር ግን መሪዎቹ ሁሉ ለማኅበሩ እንዲህ ሲሉ መለሱ፤ ‘በእስራኤል አምላክ በእግዚአብሔር ስም ስለማልንላቸው፣ አሁን ጒዳት ልናደርስባቸው አንችልም፤