1 ከዚያም ሙሴና እስራኤላውያን ይህን መዝሙር ለእግዚአብሔር (ያህዌ) ዘመሩ፤“ከፍ ከፍ ብሎ ከብሮአልና፣ ለእግዚአብሔር (ያህዌ) እዘምራለሁ፤ፈረሱንና ፈረሰኛውን፣በባሕር ውስጥ ጥሎአልና።
2 ለእግዚአብሔር (ያህዌ) ብርታቴና ዝማሬዬ ነው፤ድነቴም ሆነልኝ፤እርሱ አምላኬ ነው፤ አመሰግነዋለሁ፤የአባቴ አምላክ (ኤሎሂም) ነው፤ እኔም ከፍ ከፍ አደርገዋለሁ።
3 ለእግዚአብሔር (ያህዌ) ተዋጊ ነው፤ስሙም እግዚአብሔር (ያህዌ) ነው።
4 የፈርዖንን ሠረገሎችና ሰራዊት፣ባሕር ውስጥ ጣላቸው፤ምርጥ የሆኑት የፈርዖን ሹማምት፣ቀይ ባሕር ውስጥ ሰጠሙ።