14 አሕዛብ ይሰማሉ፤ ይንቀጠቀጡማል፤የፍልስጥኤምን ሕዝብ ሥቃይ ይይዛቸዋል።
15 የኤዶምም አለቆች ይርዳሉ፤የሞአብ አለቆች በእንቅጥቃጤ ይያዛሉ፤የከነዓን ሕዝብ ይቀልጣሉ።
16 አቤቱ እግዚአብሔር (ያህዌ) ሆይ፤ ሕዝብህእስከሚያልፉ ድረስ፣የተቤዠኻቸው ሕዝብህ እስኪያልፉ ድረስ፣ድንጋጤና ሽብር በእነርሱ ላይ ይመጣል፤በክንድህ ብርታት፣እንደ ድንጋይ የማይንቀሳቀሱ ይሆናሉ።
17 እግዚአብሔር (ያህዌ) ሆይ፤ ማደሪያህእንዲሆን በሠራኸው ስፍራ፣ጌታ (አዶናይ) ሆይ፤ እጆችህ በሠሩት መቅደስ፣በርስትህ ተራራ ላይ፣ ታመጣቸዋለህ፤ ትተክላቸዋለህም።
18 እግዚአብሔር (ያህዌ)፣ከዘላለም እስከ ዘላለም ይነግሣል።”
19 የፈርዖን ፈረሶች፣ ሠረገሎቹና ፈረሰኞቹ ወደ ባሕሩ በገቡ ጊዜ እግዚአብሔር (ያህዌ) የባሕሩን ውሃ በላያቸው ላይ መለሰባቸው፤ እስራኤላውያን ግን በባሕሩ ውስጥ በደረቅ ምድር ተሻገሩ።
20 ከዚያም የአሮን እኅት ነቢይቱ ማርያም ከበሮዋን አንሥታ ያዘች፤ የቀሩትም ሴቶች ሁሉ ከበሮ ይዘው እያሸበሸቡ ተከተሏት።