20 “አንድ ሰው ወንድ ወይም ሴት ባሪያውን በዱላ ቢመታና ባሪያውም በዚህ የተነሣ ቢሞት መቀጣት አለበት፤
21 ነገር ግን ከአንድ ወይም ከሁለት ቀን በኋላ ባሪያው ቢነሣ መቀጣት የለበትም፤ ባሪያው ንብረቱ ነውና።
22 “በጥል ላይ ያሉ ሰዎች ነፍሰ ጡር ሴት ቢመቱና እርሷም ያለጊዜዋ ብትወልድ፣ ጉዳቱም ለክፉ የማይሰጥ ቢሆን፣ ጉዳት ያደረ ሰባት ሰው የሴትዮዋ ባል የጠየቀውንና ፈራጆቹ የፈቀዱትን ካሣ ሁሉ መክፈል አለበት።
23 ነገር ግን የከፋ ጉዳት ቢደርስ ሕይወት በሕይወት፣
24 ዓይን በዓይን፣ ጥርስ በጥርስ፣ እጅ በእጅ፣ እግር በግር፣
25 ቃጠሎ በቃጠሎ፣ ቍስል በቍስል፣ ግርፋት በግርፋት ታስከፍላለህ።
26 “አንድ ሰው የወንድ ወይም የሴት አገልጋዩን ዐይን መትቶ ቢያጠፋ፣ ስለ ዐይን ካሣ አገልጋዩን ነጻ ይልቀቀው።