3 ነገር ግን ፀሓይ ከወጣች በኋላ ከተፈጸመ፣ ሰውየው በነፍስ ግድያ ይጠየቃል።“ሌባ የሰረቀውን መክፈል አለበት፤ ምንም ከሌለው ግን የሰረቀውን ይከፍል ዘንድ ይሸጥ።
4 “የሰረቀው እንስሳ በሬ ወይም አህያ፣ ወይም በግ ከነሕይወቱ በእጁ ከተያዘ እጥፍ መክፈል አለበት።
5 “አንድ ሰው ከብቶቹን በመስክ ወይም በወይን ቦታ አሰማርቶ እንዲሁ ስድ ቢለቃቸውና የሌላውን ሰው መስክ ቢግጡ፣ ምርጥ ከሆነው ከራሱ መስክ ወይም የወይን ቦታ መክፈል አለበት።
6 “እሳት ተነሥቶ ወደ ቍጥቋጦ ቢዘምትና ክምርን ወይም ያልታጨደን እህል ወይም አዝመራውን እንዳለ ቢበላ፣ እሳቱን ያቀጣጠለው ሰው ካሣ ይክፈል።
7 “አንድ ሰው ብሩ ወይም ንብረቱ ያለ ሥጋት ይጠበቅለት ዘንድ ለጎረቤቱ ሰጥቶ ሳለ ቢሰርቅበትና፣ ሌባው ቢያዝ እጥፍ ይክፈል፤
8 ሌባው ካልተያዘ ግን፣ የቤቱ ባለቤት በንብረቱ ስርቆት ላይ እጁ ይኑርበት ወይም አይኑርበት ይታወቅ ዘንድ ዳኞች ፊት ይቅረብ።
9 አንድ ሰው በሬን፣ አህያን፣ በግን፣ ልብስን፣ ወይም ማናቸውንም ንብረት ያለ አግባብ በባለቤትነት ይዞ ሳለ፣ ‘የኔ ነው’ ባይ ቢመጣና ክርክር ቢነሣ፣ ባለ ጉዳዮቹ ነገሩን ለዳኞች ያቅርቡት፤ ዳኞቹ ጥፋተኛ ነው ያሉትም ለጎረቤቱ እጥፉን ይክፈል።