7 ከዚያም የኪዳኑን መጽሐፍ ወስዶ ለሕዝቡ አነበበላቸው፤ እነርሱም፣ “እግዚአብሔር (ያህዌ) ያለውን ሁሉ እናደርጋለን፤ እንታዘዛለን” አሉ።
8 ከዚያም ሙሴ ደሙን ወሰደ፤ ሕዝቡም ላይ ረጭቶ፣ “ይህ እነዚህን ቃሎች በሰጠ ጊዜ፣ እግዚአብሔር (ያህዌ) ከእናንተ ጋር የገባው የቃል ኪዳኑ ደም ነው” አላቸው።
9 ሙሴና አሮን፣ ናዳብና አብድዩ እንደዚሁም ሰባዎቹ የእስራኤል አለቆች ወደ ተራራው ወጡ፣
10 የእስራኤልንም አምላክ (ኤሎሂም) አዩ፤ ከእግሩም በታች እንደ ብሩህ ሰማይ የጠራ የሰንፔር ወለል ነበር።
11 ሆኖም እግዚአብሔር (ኤሎሂም) በእስራኤል ሕዝብ አለቆች ላይ እጁን አላነሣባቸውም። እግዚአብሔርን (ኤሎሂም) አዩ፣ በሉ፤ ጠጡም።
12 እግዚአብሔር (ያህዌ) ሙሴን፣ “በተራራው ላይ ወደ እኔ ና፤ በዚህም ቆይ፤ እኔም መመሪያ እንዲሆናቸው ሕግና ትእዛዛት የጻፍኩባቸውን የድንጋይ ጽላቶች እሰጥሃለሁ” አለው።
13 ከዚያም ሙሴ ከረዳቱ ከኢያሱ ጋር አብሮ ሄደ፤ ሙሴም ወደ እግዚአብሔር (ኤሎሂም) ተራራ ወጣ።