16 በትውልዳቸው መሠረት የሌዊ ወንዶች ልጆች ስሞች እነዚህ ነበሩ፤ ጌድሶን፣ ቀዓትና ሜራሪ ናቸው፤ ሌዊ መቶ ሠላሳ ሰባት ዓመት ኖረ።
17 የጌድሶን ወንዶች ልጆች በትውልዳቸው ሎቤኒና ሰሜኢ ነበሩ።
18 የቀዓት ወንዶች ልጆች እንበረም፣ ይስዓር፣ ኬብሮንና ዑዝኤል ነበሩ፤ ቀዓት መቶ ሠላሳ ዓመት ኖረ።
19 የሜራሪ ወንዶች ልጆች ሞሖሊና ሙሲ ነበሩ። በትውልዳቸው መሠረት የሌዊ ነገዶች እነዚህ ናቸው።
20 እንበረም የአጎቱን እናት ዮካብድን አገባ፤ እርሷም አሮንና ሙሴን ወለደችለት። እንበረም መቶ ሠላሳ ሰባት ዓመት ኖረ።
21 የይስዓር ወንዶች ልጆች፣ ቆሬ፣ ናፌግና ዝክሪ ነበሩ።
22 የዑዝኤል ወንዶች ልጆች፣ ሚሳኤል፣ ኤልዳፋንና ሥትሪ ነበሩ።