1 ከዚያም እግዚአብሔር (ያህዌ) ሙሴን አለው፤ “ወደ ፈርዖን ዘንድ ሄደህ፣ እንዲህ በለው፤ ‘እግዚአብሔር (ያህዌ) የሚለው ይህ ነው፤ “እኔን ያመልኩኝ ዘንድ ሕዝቤን ልቀቅ።
2 እነርሱን ለመልቀቅ እምቢ ብትል አገርህን ሁሉ በጓጒንቸር መቅሠፍት እመታዋለሁ።
3 አባይ በጓጒንቸሮች ይሞላል፤ ወጥተውም ወደ ቤተ መንግሥትህና ወደ መኝታ ክፍልህ፣ ወደ አልጋህም ወደ ሹማምቶችህና ወደ ሕዝብህ ቤቶች፣ ወደ ምድጆችህና ወደ ቡሃቃዎችህ ይገባሉ።
4 ጓጒንቸሮቹ ወደ አንተና ወደ ሕዝብህ ወደ ሹማምቶችህም ሁሉ ይመጡባችኋል።’ ”
5 ከዚያም እግዚአብሔር (ያህዌ) ሙሴን አለው፣ “አሮንን፣ ‘በትርህን ይዘህ በምንጮች፣ በቦዮችና በኩሬዎች ላይ እጅህን ዘርጋ፤ ጓጒንቸሮችም በግብፅ ምድር ላይ እንዲወጡ አድርግ’ ” በለው።