1 እግዚአብሔር (ያህዌ) አብራምን እንዲህ አለው፤ “አገርህን፣ ወገንህንና የአባትህን ቤት ትተህ እኔ ወደማሳይህ ምድር ሂድ።
2 “ታላቅ ሕዝብ አደርግሃለሁ፤ደግሞም እባርክሃለሁ፤ስምህን ገናና አደርገዋለሁ፤ለሌሎች በረከት ትሆናለህ።
3 የሚባርኩህን እባርካለሁ፤የሚረግሙህን እረግማለሁ፤በምድር የሚኖሩ ሕዝቦች፣በአንተ አማካይነት ይባረካሉ።”
4 ስለዚህ አብራም እግዚአብሔር (ያህዌ) እንዳዘዘው ወጣ፤ ሎጥም አብሮት ሄደ። አብራም ከካራን ሲወጣ ዕድሜው 75 ዓመት ነበረ።
5 አብራምም ሚስቱን ሦራንና የወንድሙን ልጅ ሎጥን አስከትሎ በካራን ሳሉ ያፈሩትን ሀብትና የነበራቸውን አገልጋዮች ይዘው በመጓዝ ከነዓን ምድር ገቡ።
6 አብራም ትልቁ የሞሬ ዛፍ እስከሚገኝበት እስከ ሴኬም ድረስ በምድሪቱ ዘልቆ ሄደ። በዚያን ጊዜ ከነዓናውያን በዚሁ ምድር ይኖሩ ነበር።
7 እግዚአብሔርም (ያህዌ) ለአብራም ተገልጦ፣ “ይህችን ምድር ለዘርህ እሰጣለሁ” አለው። እርሱም ለተገለጠለት አምላክ (ያህዌ) በዚያ ስፍራ መሠዊያ ሠራ።