1 ኢየሱስ ወደ ኢያሪኮ ገብቶ በዚያ አልፎ ይሄድ ነበር።
2 ስሙ ዘኬዎስ የተባለ አንድ ሰው በዚያ ነበረ፤ ዋና ቀረጥ ሰብሳቢና ሀብታም ነበረ።
3 እርሱም ኢየሱስ የተባለው የትኛው እንደሆነ ሊያይ ይፈልግ ነበር፤ ቁመቱ አጭር ነበረና ከሕዝቡ ብዛት የተነሣ ሊያየው አልቻለም።
4 ኢየሱስ በዚያ መንገድ ያልፍ ስለ ነበርም፣ ሊያየው ወደ ፊት ሮጦ አንድ ሾላ ዛፍ ላይ ወጣ።