Bible
Now
Toggle navigation
ምዕራፎች
9
1
2
3
4
5
6
7
8
9
10
11
12
13
14
15
16
17
18
19
20
21
22
23
24
መጽሐፍት
ብሉይ ኪዳን
ዘፍጥረት
ዘፀአት
ዘሌዋውያን
ዘኁልቍ
ዘዳግም
ኢያሱ
መሳፍንት
ሩት
1 ሳሙኤል
2 ሳሙኤል
1 ነገሥት
2 ነገሥት
1 ዜና መዋዕል
2 ዜና መዋዕል
ዕዝራ
ነህምያ
አስቴር
ኢዮብ
መዝሙር
ምሳሌ
መክብብ
ማሕልየ መሓልይ
ኢሳይያስ
ኤርምያስ
ሰቆቃወ
ሕዝቅኤል
ዳንኤል
ሆሴዕ
ኢዩኤል
አሞጽ
አብድዩ
ዮናስ
ሚክያስ
ናሆም
ዕንባቆም
ሶፎንያስ
ሐጌ
ዘካርያስ
ሚልክያስ
አዲስ ኪዳን
ማቴዎስ
ማርቆስ
ሉቃስ
ዮሐንስ
ሐዋርያት ሥራ
ሮሜ
1 ቆሮንቶስ
2 ቆሮንቶስ
ገላትያ
ኤፌሶን
ፊልጵስዩስ
ቈላስይስ
1 ተሰሎንቄ
2 ተሰሎንቄ
1 ጢሞቴዎስ
2 ጢሞቴዎስ
ቲቶ
ፊልሞና
ዕብራውያን
ያዕቆብ
1 ጴጥሮስ
2 ጴጥሮስ
1 ዮሐንስ
2 ዮሐንስ
3 ዮሐንስ
ይሁዳ
ራእይ
መጽሐፍ ዝርዝር
NASV
መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
AM
Afrikaans (AF)
Avañe’ẽ (GN)
Bahasa Indonesia (ID)
Bahasa Melayu (MS)
Basa Jawa (JV)
Bokmål (NB)
Català (CA)
ChiCheŵa (NY)
ChiShona (SN)
Cymraeg (CY)
Dansk (DA)
Deutsch (DE)
Eesti (ET)
English (EN)
Español (ES)
Euskara (EU)
Français (FR)
Gaeilge (GA)
Gagana fa’a Sāmoa (SM)
Hausa (HA)
Hrvatski (HR)
Igbo (IG)
IsiXhosa (XH)
IsiZulu (ZU)
Italiano (IT)
Kiswahili (SW)
Latine (LA)
Latviešu (LV)
Lietuvių (LT)
Magyar (HU)
Malagasy (MG)
Nederlands (NL)
Nynorsk (NN)
Polski (PL)
Português (PT)
Română (RO)
Sesotho (ST)
Shqip (SQ)
Slovenčina (SK)
Slovenščina (SL)
Soomaali (SO)
Suomi (FI)
Svenska (SV)
Tagalog (TL)
Cebuano (CEB)
Tiếng Việt (VI)
Türkçe (TR)
Èdè Yorùbá (YO)
čeština (CS)
Ελληνικά (EL)
Српски (SR)
български (BG)
македонски (MK)
монгол (MN)
русский (RU)
українська (UK)
Հայերէն (HY)
עברית (HE)
اردو (UR)
العربية (AR)
سنڌي (SD)
فارسی (FA)
हिन्दी (HI)
বাংলা (BN)
தமிழ் (TA)
ไทย (TH)
မြန်မာဘာသာ (MY)
አማርኛ (AM)
ភាសាខ្មែរ (KM)
日本語 (JA)
简体中文 (ZH)
繁體中文 (ZH-HANT)
한국어 (KO)
☽
Enable dark mode
ምዕራፎች
9
1
2
3
4
5
6
7
8
9
10
11
12
13
14
15
16
17
18
19
20
21
22
23
24
መጽሐፍት
ብሉይ ኪዳን
ዘፍጥረት
ዘፀአት
ዘሌዋውያን
ዘኁልቍ
ዘዳግም
ኢያሱ
መሳፍንት
ሩት
1 ሳሙኤል
2 ሳሙኤል
1 ነገሥት
2 ነገሥት
1 ዜና መዋዕል
2 ዜና መዋዕል
ዕዝራ
ነህምያ
አስቴር
ኢዮብ
መዝሙር
ምሳሌ
መክብብ
ማሕልየ መሓልይ
ኢሳይያስ
ኤርምያስ
ሰቆቃወ
ሕዝቅኤል
ዳንኤል
ሆሴዕ
ኢዩኤል
አሞጽ
አብድዩ
ዮናስ
ሚክያስ
ናሆም
ዕንባቆም
ሶፎንያስ
ሐጌ
ዘካርያስ
ሚልክያስ
አዲስ ኪዳን
ማቴዎስ
ማርቆስ
ሉቃስ
ዮሐንስ
ሐዋርያት ሥራ
ሮሜ
1 ቆሮንቶስ
2 ቆሮንቶስ
ገላትያ
ኤፌሶን
ፊልጵስዩስ
ቈላስይስ
1 ተሰሎንቄ
2 ተሰሎንቄ
1 ጢሞቴዎስ
2 ጢሞቴዎስ
ቲቶ
ፊልሞና
ዕብራውያን
ያዕቆብ
1 ጴጥሮስ
2 ጴጥሮስ
1 ዮሐንስ
2 ዮሐንስ
3 ዮሐንስ
ይሁዳ
ራእይ
መጽሐፍ ዝርዝር
NASV
መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
AM
Afrikaans (AF)
Avañe’ẽ (GN)
Bahasa Indonesia (ID)
Bahasa Melayu (MS)
Basa Jawa (JV)
Bokmål (NB)
Català (CA)
ChiCheŵa (NY)
ChiShona (SN)
Cymraeg (CY)
Dansk (DA)
Deutsch (DE)
Eesti (ET)
English (EN)
Español (ES)
Euskara (EU)
Français (FR)
Gaeilge (GA)
Gagana fa’a Sāmoa (SM)
Hausa (HA)
Hrvatski (HR)
Igbo (IG)
IsiXhosa (XH)
IsiZulu (ZU)
Italiano (IT)
Kiswahili (SW)
Latine (LA)
Latviešu (LV)
Lietuvių (LT)
Magyar (HU)
Malagasy (MG)
Nederlands (NL)
Nynorsk (NN)
Polski (PL)
Português (PT)
Română (RO)
Sesotho (ST)
Shqip (SQ)
Slovenčina (SK)
Slovenščina (SL)
Soomaali (SO)
Suomi (FI)
Svenska (SV)
Tagalog (TL)
Cebuano (CEB)
Tiếng Việt (VI)
Türkçe (TR)
Èdè Yorùbá (YO)
čeština (CS)
Ελληνικά (EL)
Српски (SR)
български (BG)
македонски (MK)
монгол (MN)
русский (RU)
українська (UK)
Հայերէն (HY)
עברית (HE)
اردو (UR)
العربية (AR)
سنڌي (SD)
فارسی (FA)
हिन्दी (HI)
বাংলা (BN)
தமிழ் (TA)
ไทย (TH)
မြန်မာဘာသာ (MY)
አማርኛ (AM)
ភាសាខ្មែរ (KM)
日本語 (JA)
简体中文 (ZH)
繁體中文 (ZH-HANT)
한국어 (KO)
☽ Dark mode
›
መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም
›
አዲስ ኪዳን
›
ሉቃስ
›
ሉቃስ 9
ሉቃስ
ምዕራፎች 9
መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም
ሉቃስ 8
ሉቃስ 10
የዐሥራ ሁለቱ ሐዋርያት መላክ
1
ኢየሱስም ዐሥራ ሁለቱን ሐዋርያት በአንድነት ጠርቶ አጋንንትን ሁሉ እንዲያወጡ፣ ደዌንም እንዲፈውሱ ኀይልና ሥልጣን ሰጣቸው፤
2
ደግሞም የእግዚአብሔርን መንግሥት እንዲሰብኩና የታመሙትን እንዲፈውሱ ላካቸው፤
3
እንዲህም አላቸው፤ “ለመንገዳችሁ በትር ቢሆን፣ ከረጢትም ቢሆን፣ እንጀራም ቢሆን፣ ገንዘብም ቢሆን፣ ሁለት ሁለት እጀ ጠባብም መያዝ አያስፈልጋችሁም።
4
ከዚያ ከተማ እስከምትወጡ ድረስ መጀመሪያ በገባችሁበት በማንኛውም ቤት ቈዩ።
5
የከተማው ሰዎች ሳይቀበሏችሁ ቀርተው ከተማቸውን ለቃችሁ ስትሄዱ፣ ምስክር እንዲሆንባቸው የእግራችሁን ትቢያ አራግፋችሁ ውጡ።”
6
እነርሱም በዚሁ መሠረት ወጥተው ወንጌልን እየሰበኩ በየቦታው ሁሉ ሕመምተኞችን እየፈወሱ በየመንደሩ ያልፉ ነበር።
7
የአራተኛው ክፍል ገዥ ሄሮድስም፣ በዚህ ጊዜ የሆነውን ነገር ሁሉ ሰምቶ በሁኔታው ተደናገረ፤ ምክንያቱም አንዳንድ ሰዎች ዮሐንስ ከሙታን እንደ ተነሣ ያወሩ ነበር፤
8
ሌሎች ኤልያስ እንደ ተገለጠ፣ ሌሎች ደግሞ ከቀድሞዎቹ ነቢያት አንዱ ከሙታን እንደ ተነሣ ይናገሩ ነበር።
9
ሄሮድስም፣ “መጥምቁ ዮሐንስን እኔው ራሴ ዐንገቱን አስቈርጬው ሞቶአል፤ ታዲያ፣ ስለ እርሱ እንዲህ ሲወራ የምሰማው ይህ ሰው ማነው?” አለ፤ በዐይኑም ሊያየው ይሻ ነበር።
ኢየሱስ አምስት ሺህ ሰዎችን መገበ
10
ሐዋርያትም ተመልሰው በመጡ ጊዜ ያደረጉትን ሁሉ ነገሩት፤ እርሱም ይዞአቸው ቤተ ሳይዳ ወደምትባል ከተማ በመሄድ ለብቻው ገለል አለ።
11
ሕዝቡም ይህንኑ ዐውቀው ተከተሉት፤ እርሱም ተቀብሎአቸው ስለ እግዚአብሔር መንግሥት ይነግራቸው ነበር፤ ፈውስ የሚያስፈልጋቸውንም ፈወሳቸው።
12
ቀኑም ሊመሽ ሲል፣ ዐሥራ ሁለቱ ወደ እርሱ ቀርበው፣ “ያለ ነው በምድረ በዳ ስለ ሆነ፣ ሕዝቡ ወደ አካባቢው መንደርና ገጠር ሄደው ማደሪያና ምግብ እንዲፈልጉ አሰናብታቸው” አሉት።
13
እርሱ ግን፣ “የሚበሉትን እናንተው ስጧቸው” አላቸው።እነርሱም፣ “ለዚህ ሁሉ ሕዝብ የሚበቃ ምግብ ሄደን ካልገዛን በስተቀር፣ እኛ ያለን ከአምስት እንጀራና ከሁለት ዓሣ አይበልጥም” አሉት፤
14
አምስት ሺህ ያህል ወንዶች በዚያ ነበሩና።ኢየሱስም ደቀ መዛሙርቱን፣ “ሕዝቡን በአምሳ በአምሳ ሰው መድባችሁ አስቀምጧቸው” አላቸው።
15
ደቀ መዛሙርቱም በታዘዙት መሠረት ሰዎቹ እንዲቀመጡ አደረጉ።
16
እርሱም አምስቱን እንጀራና ሁለቱን ዓሣ ይዞ ወደ ሰማይ አሻቅቦ እያየ ባረካቸው፤ ቈርሶም ለሕዝቡ እንዲያቀርቡ ለደቀ መዛሙርቱ ሰጠ።
17
ሁሉም በልተው ጠገቡ፤ ደቀ መዛሙርቱም ከእነርሱ የተረፈውን ቊርስራሽ እንጀራ ዐሥራ ሁለት መሶብ አነሡ።
ጴጥሮስ ስለ ኢየሱስ ማንነት መሰከረ
18
ከዚህ በኋላ ኢየሱስ ብቻውን ይጸልይ ነበር፤ ደቀ መዛሙርቱም ከእርሱ ጋር ነበሩ፤ እርሱም፣ “ሕዝቡ እኔን ማን ነው ይሉኛል?” ብሎ ጠየቃቸው።
19
እነርሱም፣ “አንዳንዶች መጥምቁ ዮሐንስ፣ ሌሎች ኤልያስ፣ ሌሎች ደግሞ ከቀድሞ ነቢያት አንዱ ከሙታን ተነሥቶአል ይላሉ” አሉት።
20
እርሱም፣ “እናንተስ ማን ነው ትሉኛላችሁ?” አላቸው።ጴጥሮስም፣ “አንተ የእግዚአብሔር መሲሕ ነህ” ሲል መለሰለት።
21
ኢየሱስም ይህን ለማንም እንዳይናገሩ አጥብቆ አስጠነቀቃቸው፤
22
ደግሞም፣ “የሰው ልጅ ብዙ መከራ መቀበል ይገባዋል፤ እንዲሁም በሽማግሌዎች፣ በካህናት አለቆችና በጸሓፍት ዘንድ መናቅ፣ መገደልና በሦስተኛውም ቀን ከሙታን መነሣት አለበት” አላቸው።
23
ከዚያም ለሁሉም እንዲህ አላቸው፤ “በኋላዬ ሊመጣ የሚፈልግ ማንም ቢኖር ራሱን ይካድ፤ መስቀሉንም በየዕለቱ ተሸክሞ ይከተለኝ፤
24
ምክንያቱም ነፍሱን ሊያድናት የሚፈልግ ሁሉ ያጠፋታል፤ ነፍሱን ስለ እኔ ብሎ የሚያጠፋት ግን ያድናታል።
25
ሰው ዓለምን ሁሉ ቢያተርፍ ነፍሱን ግን ቢያጠፋ ወይም ቢያጐድል ጥቅሙ ምንድን ነው?
26
ማንም በእኔና በቃሌ ቢያፍር፣ የሰው ልጅ በራሱ ክብር እንዲሁም በአብና በቅዱሳን መላእክት ክብር ሲመጣ ያፍርበታል።
27
እውነት እላችኋለሁ፤ እዚህ ከቆሙት መካከል የእግዚአብሔርን መንግሥት ሳያዩ ሞትን የማይቀምሱ ሰዎች አሉ።”
የኢየሱስ መልክ መለወጥ
28
ኢየሱስ ይህን ከተናገረ ከስምንት ቀን ያህል በኋላ ጴጥሮስን፣ ዮሐንስንና ያዕቆብን ይዞ ሊጸልይ ወደ አንድ ተራራ ወጣ።
29
በመጸለይ ላይ እንዳለም የፊቱ መልክ ተለወጠ፤ ልብሱም እንደ መብረቅ የሚያንጸባርቅ ነጭ ሆነ።
30
እነሆ፤ ሁለት ሰዎች፣ እነርሱም ሙሴና ኤልያስ ከእርሱ ጋር ይነጋገሩ ነበር፤
31
በክብርም ተገልጠው፣ በኢየሩሳሌም ይፈጸም ዘንድ ስላለው ከዚህ ዓለም ስለ መለየቱ ይናገሩ ነበር።
32
ጴጥሮስና አብረውት የነበሩት ግን እንቅልፍ ተጭኖአቸው ነበር፤ ሲነቁ ግን ክብሩንና ከእርሱ ጋር የቆሙትን ሁለት ሰዎች አዩ።
33
ሰዎቹም ከኢየሱስ ተለይተው ሲሄዱ፣ ጴጥሮስ፣ “ጌታ ሆይ፤ እዚህ ብንሆን ለእኛ መልካም ነው፤ ስለዚህ ሦስት ዳስ እንሥራ፤ አንዱ ለአንተ፣ አንዱ ለሙሴ፣ አንዱም ለኤልያስ ይሆናል” አለው፤ የሚናገረውንም አያውቅም ነበር።
34
ይህንም እየተናገረ ሳለ ደመና መጥቶ ጋረዳቸው፤ ወደ ደመናውም ሲገቡ ፈሩ።
35
ከደመናውም ውስጥ፣ “የመረጥሁት ልጄ ይህ ነው፤ እርሱን ስሙት” የሚል ድምፅ መጣ።
36
ድምፁም በተሰማ ጊዜ ኢየሱስ ብቻውን ሆኖ ተገኘ፤ ደቀ መዛሙርቱም ነገሩን በልባቸው ያዙ እንጂ ስላዩት ነገር በዚያን ወቅት ለማንም አልተናገሩም።
ኢየሱስ ርኩስ መንፈስ ያለበትን ልጅ ፈወሰ
37
በማግሥቱ ከተራራው ከወረዱ በኋላ፣ ብዙ ሕዝብ መጥቶ ኢየሱስን አገኘው።
38
በዚህ ጊዜ ከሕዝቡ መካከል አንድ ሰው ድምፁን ከፍ አድርጎ እንዲህ አለ፤ “መምህር ሆይ፤ ያለኝ ልጅ እርሱ ብቻ ስለ ሆነ ልጄን እንድታይልኝ እለምንሃለሁ።
39
መንፈስ ሲይዘው በድንገት ይጮኻል፤ አረፋ እያስደፈቀው ያንፈራግጠዋል፤ ጒዳትም ካደረሰበት በኋላ በስንት መከራ ይተወዋል፤
40
ደቀ መዛሙርትህ እንዲያወጡለት ለመንኋቸው፤ ነገር ግን አልቻሉም።”
41
ኢየሱስም “እምነት የለሽ ጠማማ ትውልድ፤ እስከ መቼ ከእናንተ ጋር እኖራለሁ? እስከ መቼስ እታገሣችኋለሁ? በል ልጅህን ወደዚህ አምጣው” አለ።
42
ልጁ በመምጣት ላይ ሳለም ጋኔኑ መሬት ላይ ጥሎ አንፈራገጠው፤ ኢየሱስ ግን ርኩሱን መንፈስ ገሥጾ ልጁን ፈወሰው፤ ለአባቱም መልሶ ሰጠው።
43
ሰዎቹም ሁሉ በእግዚአብሔር ታላቅነት ተገረሙ።እርሱ ባደረገው ሁሉ ሰዎች ሁሉ እየተገረሙ ሳሉ፣ ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱን፣
44
“ይህን የምነግራችሁን ነገር ከቶ እንዳትዘነጉ፤ የሰው ልጅ አልፎ በሰዎች እጅ ይሰጣልና” አለ።
45
እነርሱ ግን ይህን አባባል አልተረዱም፤ እንዳያስተውሉ ነገሩ ተሰውሮባቸው ነበር፤ መልሰው እንዳይጠይቁትም ፈሩ።
ከሁሉ የሚበልጥ ማን ይሆን?
46
ከእነርሱ ማን እንደሚበልጥ በደቀ መዛሙርቱ መካከል ክርክር ተነሣ።
47
ኢየሱስም የልባቸውን ሐሳብ ተረድቶ፣ አንድ ሕፃን ይዞ በአጠገቡ አቆመ፤
48
እንዲህም አላቸው፤ “ይህን ሕፃን በስሜ የሚቀበል ማንም ቢኖር እኔን ይቀበላል፤ እኔን የሚቀበል ደግሞ የላከኝን ይቀበላል፤ ከሁላችሁ የሚያንስ እርሱ ከሁሉ ይበልጣልና።”
49
ዮሐንስም፣ “ጌታ ሆይ፤ አንድ ሰው በስምህ አጋንንት ሲያወጣ አየን፤ ከእኛ ጋር ሆኖ ስለ ማይከተል ልንከለክለው ሞከርን” አለው።
50
ኢየሱስም፣ አትከልክሉት “የማይቃወማችሁ ሁሉ እርሱ ከእናንተ ጋር ነውና” አለው።
የሰማርያ ሰዎች ተቃውሞ
51
ኢየሱስ ወደ ሰማይ የሚያርግበት ጊዜ በመቃረቡ፣ ወደ ኢየሩሳሌም ለመሄድ ቈርጦ ተነሣ፤
52
አስቀድሞም መልእክተኞችን ወደዚያ ላከ። እነርሱም ሁኔታዎችን አስቀድመው ሊያመቻቹለት ወደ አንድ የሳምራውያን መንደር ገቡ።
53
ሕዝቡ ግን ወደ ኢየሩሳሌም እያመራ መሆኑን ስላወቁ አልተቀበሉትም።
54
ደቀ መዛሙርቱም ያዕቆብና ዮሐንስ ይህን ሲያዩ፣ “ጌታ ሆይ፤ ኤልያስ እንዳደረገው ሁሉ እሳት ከሰማይ ወርዶ እንዲያጠፋቸው እንድናዝ ትፈቅዳለህን?” አሉት።
55
ኢየሱስ ግን ዘወር ብሎ ገሠጻቸውና “እናንተ ከምን ዐይነት መንፈስ እንደሆናችሁ አታውቁም፤ የሰው ልጅ የመጣው የሰውን ሕይወት ለማዳን ነው እንጂ ለማጥፋት አይደለምና” አላቸው፤
56
ወደ ሌላ መንደርም ሄዱ።
ደቀ መዝሙርነት የሚያስከፍለው ዋጋ
57
በመንገድ ሲሄዱም አንድ ሰው ቀርቦ፣ “ወደምትሄድበት ሁሉ እከተልሃለሁ” አለው።
58
ኢየሱስም፣ “ቀበሮዎች ጒድጓድ፣ የሰማይ ወፎችም ጎጆ አላቸው፤ የሰው ልጅ ግን ዐንገቱን እንኳ የሚያስገባበት የለውም” አለው።
59
ሌላውን ሰው ግን፣ “ተከተለኝ” አለው።ሰውየውም፣ “ጌታ ሆይ፤ አስቀድሜ ልሂድና አባቴን ልቅበር” አለው።
60
ኢየሱስም፣ “ሙታን ሙታናቸውን እንዲቀብሩ ተዋቸው፤ አንተ ግን ሄደህ የእግዚአብሔርን መንግሥት ስበክ” አለው።
61
ሌላ ሰው ደግሞ፣ “ጌታ ሆይ፤ መከተልስ እከተልሃለሁ፤ ነገር ግን ልመለስና መጀመሪያ የቤቴን ሰዎች እንድሰናበት ፍቀድልኝ” አለ።
62
ኢየሱስ ግን፣ “ዕርፍ ጨብጦ ወደ ኋላ የሚመለከት ሰው ለእግዚአብሔር መንግሥት የተገባ አይደለም” አለው።
ሉቃስ 8
ሉቃስ 10
ምዕራፎች
1
2
3
4
5
6
7
8
9
10
11
12
13
14
15
16
17
18
19
20
21
22
23
24