Bible
Now
Toggle navigation
ምዕራፎች
20
1
2
3
4
5
6
7
8
9
10
11
12
13
14
15
16
17
18
19
20
21
22
23
24
መጽሐፍት
ብሉይ ኪዳን
ዘፍጥረት
ዘፀአት
ዘሌዋውያን
ዘኁልቍ
ዘዳግም
ኢያሱ
መሳፍንት
ሩት
1 ሳሙኤል
2 ሳሙኤል
1 ነገሥት
2 ነገሥት
1 ዜና መዋዕል
2 ዜና መዋዕል
ዕዝራ
ነህምያ
አስቴር
ኢዮብ
መዝሙር
ምሳሌ
መክብብ
ማሕልየ መሓልይ
ኢሳይያስ
ኤርምያስ
ሰቆቃወ
ሕዝቅኤል
ዳንኤል
ሆሴዕ
ኢዩኤል
አሞጽ
አብድዩ
ዮናስ
ሚክያስ
ናሆም
ዕንባቆም
ሶፎንያስ
ሐጌ
ዘካርያስ
ሚልክያስ
አዲስ ኪዳን
ማቴዎስ
ማርቆስ
ሉቃስ
ዮሐንስ
ሐዋርያት ሥራ
ሮሜ
1 ቆሮንቶስ
2 ቆሮንቶስ
ገላትያ
ኤፌሶን
ፊልጵስዩስ
ቈላስይስ
1 ተሰሎንቄ
2 ተሰሎንቄ
1 ጢሞቴዎስ
2 ጢሞቴዎስ
ቲቶ
ፊልሞና
ዕብራውያን
ያዕቆብ
1 ጴጥሮስ
2 ጴጥሮስ
1 ዮሐንስ
2 ዮሐንስ
3 ዮሐንስ
ይሁዳ
ራእይ
መጽሐፍ ዝርዝር
NASV
መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
AM
Afrikaans (AF)
Avañe’ẽ (GN)
Bahasa Indonesia (ID)
Bahasa Melayu (MS)
Basa Jawa (JV)
Bokmål (NB)
Català (CA)
ChiCheŵa (NY)
ChiShona (SN)
Cymraeg (CY)
Dansk (DA)
Deutsch (DE)
Eesti (ET)
English (EN)
Español (ES)
Euskara (EU)
Français (FR)
Gaeilge (GA)
Gagana fa’a Sāmoa (SM)
Hausa (HA)
Hrvatski (HR)
Igbo (IG)
IsiXhosa (XH)
IsiZulu (ZU)
Italiano (IT)
Kiswahili (SW)
Latine (LA)
Latviešu (LV)
Lietuvių (LT)
Magyar (HU)
Malagasy (MG)
Nederlands (NL)
Nynorsk (NN)
Polski (PL)
Português (PT)
Română (RO)
Sesotho (ST)
Shqip (SQ)
Slovenčina (SK)
Slovenščina (SL)
Soomaali (SO)
Suomi (FI)
Svenska (SV)
Tagalog (TL)
Cebuano (CEB)
Tiếng Việt (VI)
Türkçe (TR)
Èdè Yorùbá (YO)
čeština (CS)
Ελληνικά (EL)
Српски (SR)
български (BG)
македонски (MK)
монгол (MN)
русский (RU)
українська (UK)
Հայերէն (HY)
עברית (HE)
اردو (UR)
العربية (AR)
سنڌي (SD)
فارسی (FA)
हिन्दी (HI)
বাংলা (BN)
தமிழ் (TA)
ไทย (TH)
မြန်မာဘာသာ (MY)
አማርኛ (AM)
ភាសាខ្មែរ (KM)
日本語 (JA)
简体中文 (ZH)
繁體中文 (ZH-HANT)
한국어 (KO)
☽
Enable dark mode
ምዕራፎች
20
1
2
3
4
5
6
7
8
9
10
11
12
13
14
15
16
17
18
19
20
21
22
23
24
መጽሐፍት
ብሉይ ኪዳን
ዘፍጥረት
ዘፀአት
ዘሌዋውያን
ዘኁልቍ
ዘዳግም
ኢያሱ
መሳፍንት
ሩት
1 ሳሙኤል
2 ሳሙኤል
1 ነገሥት
2 ነገሥት
1 ዜና መዋዕል
2 ዜና መዋዕል
ዕዝራ
ነህምያ
አስቴር
ኢዮብ
መዝሙር
ምሳሌ
መክብብ
ማሕልየ መሓልይ
ኢሳይያስ
ኤርምያስ
ሰቆቃወ
ሕዝቅኤል
ዳንኤል
ሆሴዕ
ኢዩኤል
አሞጽ
አብድዩ
ዮናስ
ሚክያስ
ናሆም
ዕንባቆም
ሶፎንያስ
ሐጌ
ዘካርያስ
ሚልክያስ
አዲስ ኪዳን
ማቴዎስ
ማርቆስ
ሉቃስ
ዮሐንስ
ሐዋርያት ሥራ
ሮሜ
1 ቆሮንቶስ
2 ቆሮንቶስ
ገላትያ
ኤፌሶን
ፊልጵስዩስ
ቈላስይስ
1 ተሰሎንቄ
2 ተሰሎንቄ
1 ጢሞቴዎስ
2 ጢሞቴዎስ
ቲቶ
ፊልሞና
ዕብራውያን
ያዕቆብ
1 ጴጥሮስ
2 ጴጥሮስ
1 ዮሐንስ
2 ዮሐንስ
3 ዮሐንስ
ይሁዳ
ራእይ
መጽሐፍ ዝርዝር
NASV
መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
AM
Afrikaans (AF)
Avañe’ẽ (GN)
Bahasa Indonesia (ID)
Bahasa Melayu (MS)
Basa Jawa (JV)
Bokmål (NB)
Català (CA)
ChiCheŵa (NY)
ChiShona (SN)
Cymraeg (CY)
Dansk (DA)
Deutsch (DE)
Eesti (ET)
English (EN)
Español (ES)
Euskara (EU)
Français (FR)
Gaeilge (GA)
Gagana fa’a Sāmoa (SM)
Hausa (HA)
Hrvatski (HR)
Igbo (IG)
IsiXhosa (XH)
IsiZulu (ZU)
Italiano (IT)
Kiswahili (SW)
Latine (LA)
Latviešu (LV)
Lietuvių (LT)
Magyar (HU)
Malagasy (MG)
Nederlands (NL)
Nynorsk (NN)
Polski (PL)
Português (PT)
Română (RO)
Sesotho (ST)
Shqip (SQ)
Slovenčina (SK)
Slovenščina (SL)
Soomaali (SO)
Suomi (FI)
Svenska (SV)
Tagalog (TL)
Cebuano (CEB)
Tiếng Việt (VI)
Türkçe (TR)
Èdè Yorùbá (YO)
čeština (CS)
Ελληνικά (EL)
Српски (SR)
български (BG)
македонски (MK)
монгол (MN)
русский (RU)
українська (UK)
Հայերէն (HY)
עברית (HE)
اردو (UR)
العربية (AR)
سنڌي (SD)
فارسی (FA)
हिन्दी (HI)
বাংলা (BN)
தமிழ் (TA)
ไทย (TH)
မြန်မာဘာသာ (MY)
አማርኛ (AM)
ភាសាខ្មែរ (KM)
日本語 (JA)
简体中文 (ZH)
繁體中文 (ZH-HANT)
한국어 (KO)
☽ Dark mode
›
መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም
›
አዲስ ኪዳን
›
ሉቃስ
›
ሉቃስ 20
ሉቃስ
ምዕራፎች 20
መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም
ሉቃስ 19
ሉቃስ 21
የኢየሱስ ሥልጣን ለአይሁድ አጠያያቂ ሆነባቸው
1
አንድ ቀን ኢየሱስ ሕዝቡን በቤተ መቅደስ ሲያስተምርና ወንጌልን ሲሰብክ የካህናት አለቆች፣ ጸሐፍትና ሽማግሌዎች ተሰብስበው ወደ እርሱ መጡ፤
2
እነርሱም፣ “እነዚህን ነገሮች የምታደርገው በምን ሥልጣን እንደሆነ ንገረን፤ ሥልጣንስ የሰጠህ ለመሆኑ እርሱ ማን ነው?” ብለው ጠየቁት።
3
እርሱም እንዲህ ሲል መለሰላቸው፤ “እኔም አንድ ጥያቄ ልጠይቃችሁ፤ እስቲ መልሱልኝ፤
4
የዮሐንስ ጥምቀት ከሰማይ ነበር ወይስ ከሰው?”
5
እነርሱም እንዲህ ብለው እርስ በርስ ተመካከሩ፤ “ ‘ከሰማይ’ ብንል፣ ‘ታዲያ፣ ለምን አላመናችሁበትም?’ ይለናል፤
6
‘ከሰው’ ብንል ሕዝቡ ሁሉ ዮሐንስ ነቢይ መሆኑን ስለ ሚያምኑ በድንጋይ ይወግሩናል።”
7
ስለዚህ፣ “ከየት እንደሆነ አናውቅም” ብለው መለሱለት።
8
ኢየሱስም፣ “እንግዲያውስ እኔም እነዚህን ነገሮች በምን ሥልጣን እንደማደርግ አልነግራችሁም” አላቸው።
የጭሰኞቹ ምሳሌ
9
ከዚህ በኋላ ኢየሱስ እንዲህ ሲል ይህን ምሳሌ ለሕዝቡ ይነግራቸው ጀመር፤ “አንድ ሰው የወይን ተክል ተከለ፤ ለገበሬዎችም አከራየና ወደ ሌላ አገር ሄዶ ብዙ ጊዜ ቈየ።
10
በመከርም ወራት፣ ከወይኑ ፍሬ እንዲልኩለት አገልጋዩን ወደ እነዚህ ገበሬዎች ላከ፤ ገበሬዎቹ ግን አገልጋዩን ደብድበው ባዶ እጁን ሰደዱት።
11
ቀጥሎም ሌላ አገልጋዩን ላከ፤ ገበሬዎቹም እርሱንም ደግሞ ደበደቡት፤ አዋርደውም ባዶ እጁን ሰደዱት።
12
አሁንም ቀጥሎ ሦስተኛ አገልጋዩን ላከ፤ ገበሬዎቹም እርሱንም ደግሞ አቊስለው ወደ ውጭ ጣሉት።
13
“የወይኑ ተክል ባለቤትም፣ ‘እንግዲህ ምን ላድርግ? እስቲ ደግሞ የምወደውን ልጄን እልካለሁ፤ ምናልባት እርሱን ያከብሩት ይሆናል’ አለ።
14
“ገበሬዎቹ ግን ልጁን ባዩት ጊዜ፣ ይህ እኮ ወራሹ ነው፣ ‘ኑና እንግደለው፤ በዚህም ርስቱ የእኛ ይሆናል’ እየተባባሉ ተመካከሩ፤
15
ከወይኑም ተክል ቦታ ወደ ውጭ አውጥተው ገደሉት። “እንግዲህ የወይኑ ተክል ባለቤት ምን ያደርጋቸዋል?
16
መጥቶ እነዚያን ገበሬዎች ያጠፋቸዋል፤ የወይኑንም ተክል ቦታ ለሌሎች ይሰጣል።”ሕዝቡም ይህን በሰሙ ጊዜ፣ “እንዲህ ያለውንስ አያምጣው” አሉ።
17
ኢየሱስም ወደ እነርሱ ተመልክቶ እንዲህ አላቸው፤ “ ‘ታዲያ ግንበኞች የናቁት ድንጋይ፣ እርሱ የማእዘን ራስ ሆነ’ ተብሎ የተጻፈው ትርጒሙ ምንድን ነው?
18
በዚህ ድንጋይ ላይ የሚወድቅ ሁሉ ይቀጠቀጣል፤ ድንጋዩም በላዩ የሚወድቅበት ሁሉ ይደቃል።”
19
ጸሐፍትና የካህናት አለቆችም ይህንን ምሳሌ የተናገረው በእነርሱ ላይ መሆኑን ስላወቁ፣ በዚያኑ ሰዓት ሊይዙት ፈልገው ነበር፤ ነገር ግን ሕዝቡን ፈሩ።
ለቄሣር ግብር መክፈል
20
ኢየሱስን አሳልፈው ለገዥው ኀይልና ሥልጣን ለመስጠት፣ ከአፉ በሚወጣ ቃል ለማጥመድ ይከታተሉት ነበር፤ ስለዚህም ጻድቃን መስለው የሚቀርቡ ሰላዮችን ላኩበት።
21
ሰላዮቹም እንዲህ ሲሉ ጠየቁት፤ “መምህር ሆይ፤ አንተ ትክክለኛውን ነገር እንደምትናገርና እንደምታስተምር እንዲሁም የእግዚአብሔርን መንገድ በእውነት እንደ ምታስተምርና ለማንም እንደማታደላ እናውቃለን።
22
ለመሆኑ ለቄሳር ግብር መክፈል ይገባል ወይስ አይገባም?”
23
እርሱ ግን ተንኰላቸውን ዐውቆ እንዲህ አላቸው፤
24
“እስቲ አንድ ዲናር አሳዩኝ፤ በላዩ ያለው የማን መልክና ጽሕፈት ነው?”
25
እነርሱም፣ “የቄሳር ነው” ብለው መለሱለት።እርሱም፣ “እንግዲያውስ የቄሳርን ለቄሳር፣ የእግዚአብሔርንም ለእግዚአብሔር ስጡ” አላቸው።
26
ስለዚህ በተናገረው ቃል በሕዝቡ ፊት ሊያጠምዱት አልቻሉም፤ በመልሱም ተገርመው ዝም አሉ።
ትንሣኤ ሙታንና ጋብቻ
27
ትንሣኤ ሙታን የለም ከሚሉት ሰዱቃውያን አንዳንዶቹ ወደ ኢየሱስ መጥተው ጥያቄ አቀረቡለት፤
28
እንዲህም አሉት፤ “መምህር ሆይ፤ አንድ ሰው ሚስት አግብቶ ልጅ ሳይወልድ ቢሞት፣ ወንድሙ መበለቲቱን አግብቶ ልጆች በመውለድ ለወንድሙ ዘር እንዲተካ ሙሴ ጽፎልናል።
29
ታዲያ፣ ሰባት ወንድማማቾች ነበሩ፤ የመጀመሪያው ሚስት አግብቶ ልጅ ሳይወልድ ሞተ፤
30
ሁለተኛውም እንደዚሁ፤
31
ሦስተኛው ደግሞ አገባት፤ ሰባቱም እንዲሁ እያሉ አግብተዋት ልጆች ሳይወልዱ ሞቱ።
32
በመጨረሻም ሴትዮዋ ሞተች።
33
እንግዲህ ሰባቱም ስላገቧት፣ በትንሣኤ ጊዜ የማን ሚስት ትሆናለች?”
34
ኢየሱስም እንዲህ ሲል መለሰላቸው፤ “የዚህ ዓለም ልጆች ያገባሉ፤ ይጋባሉም፤
35
የሚመጣውን ዓለምና የሙታንን ትንሣኤ ማግኘት የሚገባቸው ግን አያገቡም፤ አይጋቡም፤
36
እንደ መላእክትም ስለሆኑ ከዚያ በኋላ አይሞቱም፤ የትንሣኤ ልጆች ስለ ሆኑም የእግዚአብሔር ልጆች ናቸው።
37
ሙሴ ስለ ቊጥቋጦ በተጻፈው ታሪክ ውስጥ ጌታን፣ ‘የአብርሃም አምላክ፣ የይስሐቅ አምላክ፣ የያዕቆብ አምላክ’ በማለቱ ሙታን እንደሚነሡ ያሳያል፤
38
ሁሉም ለእርሱ ሕያዋን ስለሆኑ፣ እርሱ የሕያዋን አምላክ እንጂ የሙታን አይ ደለም።”
39
አንዳንድ ጸሐፍትም፣ “መምህር ሆይ፤ መልካም ተናገርህ” አሉት።
40
ከዚህ በኋላ አንድ ሰው እንኳ ሊጠይቀው አልደፈረም።
ክርስቶስ የማን ልጅ ነው?
41
ከዚህ በኋላ ኢየሱስ እንዲህ አላቸው፤ “ሰዎች ክርስቶስን እንዴት የዳዊት ልጅ ነው ይሉታል?
42
ምክንያቱም ራሱ ዳዊት በመዝሙራት መጽሐፉ እንዲህ ብሏል፤ “ ‘ጌታ ጌታዬን፣ “በቀኜ ተቀመጥ፤
43
እኔ ጠላቶችህን፣ ለእግርህ መርገጫ እስከማደርግልህ ድረስ።” ’
44
እንግዲህ ዳዊት እርሱን፣ ‘ጌታ’ ብሎ ሲጠራው እንዴት ልጁ ይሆናል?”
45
ሕዝቡ ሁሉ እየሰሙትም ለደቀ መዛሙርቱ እንዲህ አላቸው፤
46
“ዘርፋፋ ቀሚስ ለብሰው መዞር ከሚወዱ፣ በገበያ ቦታ ሰላምታ ከሚሹና በምኵራብ የከበሬታ መቀመጫ፣ በግብዣ ቦታም የክብር ስፍራ ከሚፈልጉ፣ ከጸሐፍት ተጠንቀቁ፤
47
እነርሱም የመበለቶችን ቤት የሚያራቊቱ ናቸው፤ ለታይታ ብለውም ጸሎታቸውን ያስረዝማሉ፤ እነዚህ የከፋ ፍርድ ይጠብቃቸዋል።”
ሉቃስ 19
ሉቃስ 21
ምዕራፎች
1
2
3
4
5
6
7
8
9
10
11
12
13
14
15
16
17
18
19
20
21
22
23
24