30 ዐይኖቼ በሰዎች ሁሉ ፊት ያዘጋጀኸውን፣
31 ማዳንህን አይተዋልና።
32 ይህም ለአሕዛብ መገለጥን የሚሰጥ ብርሃን፣ለሕዝብህ ለእስራኤልም ክብር ነው።”
33 አባቱና እናቱም ስለ እርሱ በተነገረው ነገር ተገረሙ።
34 ስምዖንም ባረካቸው፤ እናቱን ማርያምንም እንዲህ አላት፤ “ይህ ሕፃን በእስራኤል ለብዙዎች መነሣትና መውደቅ ምክንያት እንዲሆን፣ ደግሞም ክፉ ለሚያስወሩበት ምልክት እንዲሆን ተወስኖአል፤
35 የብዙዎችም የልብ ሐሳብ የተገለጠ እንዲሆን፣ የአንቺም ነፍስ ደግሞ በሰይፍ ይወጋል።”
36 ደግሞም ከአሴር ወገን የሆነች የፋኑኤል ልጅ፣ ሐና የምትባል ነቢይት በዚያ ነበረች፤ እርሷም በጣም አርጅታ ነበር፤ በድንግልናዋ ካገባችው ባሏም ጋር ሰባት ዓመት የኖረች ነበረች፤