40 ከዚህ በኋላ አንድ ሰው እንኳ ሊጠይቀው አልደፈረም።
41 ከዚህ በኋላ ኢየሱስ እንዲህ አላቸው፤ “ሰዎች ክርስቶስን እንዴት የዳዊት ልጅ ነው ይሉታል?
42 ምክንያቱም ራሱ ዳዊት በመዝሙራት መጽሐፉ እንዲህ ብሏል፤ “ ‘ጌታ ጌታዬን፣ “በቀኜ ተቀመጥ፤
43 እኔ ጠላቶችህን፣ ለእግርህ መርገጫ እስከማደርግልህ ድረስ።” ’
44 እንግዲህ ዳዊት እርሱን፣ ‘ጌታ’ ብሎ ሲጠራው እንዴት ልጁ ይሆናል?”
45 ሕዝቡ ሁሉ እየሰሙትም ለደቀ መዛሙርቱ እንዲህ አላቸው፤
46 “ዘርፋፋ ቀሚስ ለብሰው መዞር ከሚወዱ፣ በገበያ ቦታ ሰላምታ ከሚሹና በምኵራብ የከበሬታ መቀመጫ፣ በግብዣ ቦታም የክብር ስፍራ ከሚፈልጉ፣ ከጸሐፍት ተጠንቀቁ፤