33 ሰማይና ምድር ያልፋሉ፤ ቃሌ ግን አያልፍም።”
34 “እንግዲህ በገደብ የለሽ ሕይወት፣ በመጠጥ ብዛትና ስለ ኑሮ በመጨነቅ ልባችሁ እንዳይዝልና ያ ቀን እንደ ወጥመድ ድንገት እንዳይደርስባችሁ ተጠንቀቁ፤
35 ይህ በመላው ምድር በሚኖሩት ሁሉ ላይ ይደርሳልና።
36 ስለዚህ ከሚመጣው ሁሉ እንድ ታመልጡና በሰው ልጅ ፊት መቆም እንድትችሉ ሁል ጊዜ ተግታችሁ ጸልዩ።”
37 ኢየሱስም ቀን ቀን በቤተ መቅደስ እያስተማረ፣ ሌሊት ግን ደብረ ዘይት ወደተባለ ተራራ ወጥቶ ያድር ነበር።
38 ሕዝቡም ሁሉ ሊሰሙት ማልደው ወደ ቤተ መቅደስ ወደ እርሱ ይመጡ ነበር።