4 ኢየሱስም፣ “ ‘ሰው በእንጀራ ብቻ አይኖርም’ ተብሎ ተጽፎአል” ብሎ መለሰለት።
5 ከዚያም ዲያብሎስ ወደ አንድ ከፍታ ቦታ አውጥቶት የዓለምን መንግሥታት ሁሉ በቅጽበት አሳየው፤
6 እንዲህም አለው፤ “የእነዚህ መንግሥታት ሥልጣንና ክብር ሁሉ ለእኔ ተሰጥቶአል፤ እኔም ለምወደው ስለምሰጥ፣ ለአንተ እሰጥሃለሁ፤
7 ስለዚህ ብትሰግድልኝ ይህ ሁሉ የአንተ ይሆናል።”
8 ኢየሱስም መልሶ፣ “ ‘ለጌታ ለአምላክህ ስገድ፤ እርሱንም ብቻ አምልክ’ ተብሎ ተጽፎአል” አለው።
9 ከዚያም ወደ ኢየሩሳሌም ወስዶ በቤተ መቅደስ ጒልላት ላይ አቆመውና እንዲህ አለው፤ “የእግዚአብሔር ልጅ ከሆንህ፣ እስቲ ራስህን ከዚህ ወደ ታች ወርውር፤
10 ምክንያቱም እንዲህ ተብሎ ተጽፎአል፤“ ‘ይጠብቁህ ዘንድ፣መላእክቱን ስለ አንተ ያዛቸዋል፤