1 ኢየሱስ ይህን ሁሉ በሕዝቡ ፊት ተናግሮ ከጨረሰ በኋላ ወደ ቅፍርናሆም ገባ።
2 በዚያም አንድ የመቶ አለቃ ነበረ፤ እጅግ የሚወደው አገልጋዩም ታሞበት ለሞት ተቃርቦ ነበር።
3 እርሱም ስለ ኢየሱስ በሰማ ጊዜ አገልጋዩን እንዲፈውስለት ይለምኑት ዘንድ አንዳንድ የአይሁድ ሽማግሌዎችን ላከበት።
4 መልእክተኞቹም ወደ ኢየሱስ በመጡ ጊዜ እንዲህ ብለው አጥብቀው ለመኑት፤ “ይህን ልታደርግለት ይገባዋል፤
5 ምክንያቱም ይህ ሰው ሕዝባችንን ይወዳል፤ ምኵራባችንንም ያሠራልን እርሱ ነው።”
6 ኢየሱስም ከእነርሱ ጋር ሄደ።እርሱም ወደ ቤቱ በተቃረበ ጊዜ፣ የመቶ አለቃው ወዳጆቹን ልኮ እንዲህ አለው፤ “ጌታ ሆይ፤ ከቤቴ ጣራ በታች ልትገባ የሚገባኝ ሰው አይደለሁምና አትድከም፤
7 ከዚህም የተነሣ በአንተ ፊት ለመቅረብ እንኳ እንደሚገባኝ ራሴን አልቈጠርሁም፤ ብቻ አንድ ቃል ተናገር፤ አገልጋዬ ይፈወሳል።