ሮሜ 16:14-20 NASV

14 ለአስቀሪጦንና ለአፍለሶንጳ፣ ለሄሮሜን፣ ለጳጥሮባን፣ ለሄርማን፣ ከእነርሱም ጋር ላሉት ወንድሞች ሰላምታ አቅርቡልኝ።

15 ለፍሌጎን፣ ለዩልያ፣ ለኔርያና ለእኅቱ፣ እንዲሁም ለአልንጦን፣ ከእነርሱም ጋር ላሉት ቅዱሳን ሰላምታ አቅርቡልኝ።

16 በተቀደሰ አሳሳም ሰላምታ ተሰጣጡ። የክርስቶስ አብያተ ክርስቲያናት ሁሉ ሰላምታ ያቀርቡላችኋል።

17 ወንድሞች ሆይ፤ መለያየትን ከሚፈጥሩትና የተማራችሁትን ትምህርት በመቃወም በጒዞአችሁ መሰናክል ከሚያደርጉት እንድትጠነቀቁ አሳስባችኋለሁ፤ ከእነርሱም ራቁ።

18 እንደ እነዚህ ያሉት ሰዎች የሚያገለግሉት ጌታችንን ኢየሱስ ክርስቶስን ሳይሆን፣ የራሳቸውን ሆድ ነው፤ በለሰለሰ አንደ በታቸውና በሽንገላ፣ የዋሆችን ያታልላሉ።

19 የእናንተን ታዛዥነት ሁሉም ሰምተዋል፤ በዚህም እኔ እጅግ ተደስቻለሁ። ሆኖም በጎ ስለ ሆነው ነገር ጥበበኞች፣ ክፉ ስለ ሆነውም የዋሆች እንድትሆኑ እፈልጋለሁ።

20 የሰላም አምላክ፣ ሰይጣንን ከእግራችሁ በታች ፈጥኖ ይቀጠቅጠዋል።የጌታችን የኢየሱስ ጸጋ ከእናንተ ጋር ይሁን።