5 የደላቸው በመከራ ያፌዛሉ፤እግሩ የተንሸራተተውንም ይገፈትራሉ።
6 የቀማኞች ድንኳን አይታወክም፤አምላካቸውን በእጃቸው ይዘው እየዞሩም፣እግዚአብሔርንም እያስቈጡ በሰላም ይኖራሉ።
7 “እስቲ እንስሶችን ጠይቁ፤ ያስተምሯችኋል፤የሰማይ ወፎችንም ጠይቁ፣ ይነግሯችኋል፤
8 ለምድር ተናገሩ፤ ታስተምራችኋለች፤የባሕርም ዓሣ ይነግራችኋል።
9 የእግዚአብሔር እጅ ይህን እንዳደረገ፣ከእነዚህ ሁሉ የማያውቅ ማን ነው?
10 የፍጥረት ሁሉ ሕይወት፣የሰውም ሁሉ መንፈስ በእጁ ናትና፤
11 ምላስ የምግብን ጣዕም እንደሚለይ፣ጆሮ ቃላትን አይለይምን?