ኢዮብ

ምዕራፎች 23

መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ኢዮብ

1ኢዮብም እንዲህ ሲል መለሰ፤ 2“ዛሬም ሐዘኔ መራራ ነው፤እያቃሰትሁ እንኳ እጁ በላዬ ከብዳለች። 3እርሱን የት እንደማገኘው ባወቅሁ፤ወደ መኖሪያውም መሄድ በቻልሁ! 4ጒዳዬን በፊቱ አቀርብ ነበር፤አፌንም በሙግት እሞላው ነበር። 5የሚመልስልኝ ቃል ምን እንደሆነ ባወቅሁ ነበር፤የሚለኝንም ባስተዋልሁ ነበር። 6በታላቅ ኀይሉ ከእኔ ጋር ይሟገት ይሆን?አይደለም፤ ይልቁን ያደምጠኛል። 7ቅን ሰው ጒዳዩን በእርሱ ፊት ያቀርባል፤እኔም ከፈራጄ ለዘላለም ነጻ እሆናለሁ። 8“ዳሩ ግን ወደ ምሥራቅ ብሄድ፣ በዚያ የለም፤ወደ ምዕራብም ብሄድ፣ እርሱን አላገኘውም፤ 9በሰሜን እየሠራ ሳለ አላየውም፤ወደ ደቡብ በሚዞርበት ጊዜ ደብዛው አይገኝም። 10ግን እኔ የምሄድበትን መንገድ ያውቃል፤ከፈተነኝም በኋላ እንደ ወርቅ እወጣለሁ። 11እግሮቼ እርምጃውን በጥብቅ ተከታትለዋል፤ፈቀቅ ሳልል መንገዱን ጠብቄአለሁ። 12ከአፉ ከወጣው ትእዛዝ አልራቅሁም፣የአንደበቱን ቃል ከዕለት እንጀራዬ አብልጬ ይዣለሁ። 13“እርሱ ግን ራሱን ችሎ ብቻውን የሚኖር ነው፤ የሚቋቋመውስ ማን ነው?እርሱ የፈቀደውን ያደርጋል። 14በእኔ ላይ የወሰነውን ይፈጽማል፤ይህን የመሰለ ዕቅድም ገና ብዙ አለው። 15በፊቱ የደነገጥሁትም ለዚህ ነው፤ይህን ሁሉ ሳስብ እፈራለሁ። 16እግዚአብሔር ልቤን አባባው፤ሁሉንም የሚችል አምላክ አስደነገጠኝ።