1 ሹሐዊውም በልዳዶስ እንዲህ ሲል መለሰ፤
2 “ገዢነትና ግርማ የእግዚአብሔር ናቸው፤በሰማይም ከፍታ ሥርዐትን ያደርጋል።
3 ሰራዊቱ ሊቈጠር ይችላልን?ብርሃኑስ የማይወጣው በማን ላይ ነው?
4 ሰው በእግዚአብሔር ፊት ጻድቅ ይሆን ዘንድ፣ከሴትስ የተወለደ ንጹሕ ይሆን ዘንድ ይችላልን?
5 በፊቱ ጨረቃ እንኳ ብሩህ ካልሆነች፣ከዋክብትም ንጹሓን ካልሆኑ፣
6 ይልቁን ከብል የሚቈጠር የሰው ልጅ፣ትል የሆነውማ ሰው ምንኛ ያንስ!”