1 “ከሴት የተወለደ ሰው፣ዘመኑ አጭርና በመከራ የተሞላ ነው፤
2 እንደ አበባ ይፈካል፤ ይረግፋልም፤እንደ ጥላ ይፈጥናል፤ አይጸናምም።
3 እንደዚህ ባለ ሰው ላይ ዐይንህን ታሳርፋለህን?ለፍርድስ በፊትህ ታቀርበዋለህን?
4 ከርኩስ ነገር ውስጥ ንጹሕን ማን ሊያወጣ ይችላል?አንድ እንኳ የሚችል የለም!
5 የሰው ዕድሜ አስቀድሞ የተወሰነ ነው፣የወራቱንም ብዛት ወስነህ አስቀምጠሃል፤ሊያልፈው የማይችለውንም ገደብ አኖርህለት።
6 እንግዲህ ዘመኑን እንደ ምንደኛ እስኪፈጽም ድረስ፣ፊትህን ከእርሱ መልስ፤ ተወው።
7 “ዛፍ እንኳ ቢቈረጥ፣እንደ ገና ሊያቈጠቍጥ፣አዳዲስ ቅርንጫፍም ሊያበቅል ተስፋ አለው።