3 በማይረባ ቃል፣ፍሬ ቢስ በሆነም ንግግር ይከራከራልን?
4 አንተ ግን እግዚአብሔርን መፍራት ታጣጥላለህ፤አምልኮተ እግዚአብሔርን ትከለክላለህ።
5 ኀጢአትህ አፍህን ታስተምረዋለች፤የተንኰለኞችንም አነጋገር መርጠህ ትይዛለህ።
6 የሚፈርድብህ አንደበትህ እንጂ እኔ አይደለሁም፣የሚመሰክርብህም እኔ ሳልሆን የገዛ ከንፈርህ ነው።
7 “ለመሆኑ ከሰው ሁሉ ቀድመህ የተወለድህ አንተ ነህን?ወይስ ከኰረብቶች በፊት ተገኝተሃል?
8 በእግዚአብሔር የመማክርት ጉባኤ ላይ ነበርህን?ጥበብስ የተሰጠው ለአንተ ብቻ ነው?
9 እኛ የማናውቀው አንተ ግን የምታውቀው ምን ነገር አለ?እኛስ የሌለን አንተ ያለህ ማስተዋል የቱ ነው?