1 ኢዮብም እንዲህ ሲል መለሰ፤
2 “ይህን የሚመስል ብዙ ነገር ሰምቻለሁ፤እናንተ ሁላችሁ የምታስጨንቁ አጽናኞች ናችሁ።
3 ይህ ከንቱ ንግግር አያልቅምን?ትለፈልፍ ዘንድ የሚገፋፋህ ምንድን ነው?
4 እናንተ በእኔ ስፍራ ብትሆኑ ኖሮ፣እኔም እንደ እናንተ መናገር እችል ነበር፤ቃላት አሳክቼ በመናገር፣በእናንተ ላይ ራሴን መነቅነቅ በቻልሁ ነበር።
5 ይልቁንም አንደበቴ ባበረታታችሁ፣የከንፈሬም ማጽናናት ባሳረፋችሁ ነበር።
6 “ብናገር ሕመሜ አይሻለኝም፤ዝም ብልም አይተወኝም።