11 ዕድሜዬ አለቀ፤ ዕቅዴም ከሸፈ፤የልቤም ሐሳብ ከንቱ ሆነ።
12 እነዚህ ሰዎች ሌሊቱን ወደ ቀን ይለውጣሉ፤ጨልሞም እያዩ፣ ‘ብርሃን ቀርቦአል’ ይላሉ።
13 ተስፋ የማደርገው ቤት መቃብር ብቻ ከሆነ፣መኝታዬንም በጨለማ ካነጠፍሁ፣
14 መበስበስን፣ ‘አንተ አባቴ ነህ፤’ትልንም፣ ‘አንቺ እናቴ’ ወይም ‘እኅቴ ነሽ’ ካልሁ፣
15 ታዲያ፣ የእኔ ተስፋ ወዴት ነው?ተስፋዬን የሚያይልኝስ ማን ነው?
16 ወደ ሞት ደጅ ይወርዳልን?አብረንስ ወደ ትቢያ እንሄዳለንን?”