1 ኢዮብም እንዲህ ሲል መለሰ፤
2 “ዛሬም ሐዘኔ መራራ ነው፤እያቃሰትሁ እንኳ እጁ በላዬ ከብዳለች።
3 እርሱን የት እንደማገኘው ባወቅሁ፤ወደ መኖሪያውም መሄድ በቻልሁ!
4 ጒዳዬን በፊቱ አቀርብ ነበር፤አፌንም በሙግት እሞላው ነበር።
5 የሚመልስልኝ ቃል ምን እንደሆነ ባወቅሁ ነበር፤የሚለኝንም ባስተዋልሁ ነበር።