8 “ዳሩ ግን ወደ ምሥራቅ ብሄድ፣ በዚያ የለም፤ወደ ምዕራብም ብሄድ፣ እርሱን አላገኘውም፤
9 በሰሜን እየሠራ ሳለ አላየውም፤ወደ ደቡብ በሚዞርበት ጊዜ ደብዛው አይገኝም።
10 ግን እኔ የምሄድበትን መንገድ ያውቃል፤ከፈተነኝም በኋላ እንደ ወርቅ እወጣለሁ።
11 እግሮቼ እርምጃውን በጥብቅ ተከታትለዋል፤ፈቀቅ ሳልል መንገዱን ጠብቄአለሁ።
12 ከአፉ ከወጣው ትእዛዝ አልራቅሁም፣የአንደበቱን ቃል ከዕለት እንጀራዬ አብልጬ ይዣለሁ።
13 “እርሱ ግን ራሱን ችሎ ብቻውን የሚኖር ነው፤ የሚቋቋመውስ ማን ነው?እርሱ የፈቀደውን ያደርጋል።
14 በእኔ ላይ የወሰነውን ይፈጽማል፤ይህን የመሰለ ዕቅድም ገና ብዙ አለው።