2 “በእግዚአብሔር የተጠበቅሁበትን ዘመን፣ያለፈውንም ወራት ምንኛ ተመኘሁ!
3 ያን ጊዜ መብራቱ በራሴ ላይ ይበራ ነበር፤በብርሃኑም በጨለማ ውስጥ ዐልፌ እሄድ ነበር፤
4 እኔም ብርቱ ነበርሁ፤የእግዚአብሔርም ወዳጅነት ቤቴን ይባርክ ነበር፤
5 ሁሉን የሚችል አምላክ ከእኔ ጋር ነበረ፤ልጆቼም በዙሪያዬ ነበሩ፤
6 መንገዴ በቅቤ የራሰ ነበር፤ዐለቱም የወይራ ዘይት ያመነጭልኝ ነበር።
7 “ወደ ከተማዪቱ በር ብቅ ባልሁ ጊዜ፣በአደባባይዋም በወንበር በተቀመጥሁ ጊዜ፣
8 ጐበዛዝት አይተውኝ ገለል ይሉ፣ሽማግሌዎችም ተነሥተው ይቆሙ ነበር።