7 “ወደ ከተማዪቱ በር ብቅ ባልሁ ጊዜ፣በአደባባይዋም በወንበር በተቀመጥሁ ጊዜ፣
8 ጐበዛዝት አይተውኝ ገለል ይሉ፣ሽማግሌዎችም ተነሥተው ይቆሙ ነበር።
9 የሰፈሩ ታላላቅ ሰዎች ከመናገር ይቈጠቡ፣እጃቸውንም በአፋቸው ላይ ይጭኑ ነበር፤
10 የመኳንንት ድምፅ ጸጥ ይል፣ምላሳቸውም ከላንቃቸው ጋር ይጣበቅ ነበር፤
11 የሰሙኝ ሁሉ ያሞጋግሱኝ፣ያዩኝም ያመሰግኑኝ ነበር፤
12 ለርዳታ የሚጮኸውን ችግረኛ፣ድኻ ዐደጉንም ታድጌአለሁና።
13 በሞት አፋፍ ላይ የነበረ መርቆኛል፤የመበለቲቱንም ልብ አሳርፌአለሁ።