16 እንግዲህ እነርሱ መልስ ስላጡ፣ጸጥ ብለውም ስለ ቆሙ፣ በትዕግሥት ልጠብቅን?
17 እኔም የምለው ይኖረኛል፤የማውቀውንም እገልጣለሁ።
18 የምናገረው ሞልቶኛልና፤በውስጤ ያለውም መንፈስ ገፋፍቶኛል።
19 ውስጤ እንደ ተከደነና መተንፈሻ እንዳጣ የወይን ጠጅ፣ሊፈነዳ እንደ ተቃረበም አዲስ የወይን ጠጅ አቁማዳ ሆኖአል።
20 ተናግሬ መተንፈስ አለብኝ፤አፌንም ከፍቼ መልስ መስጠት ይገባኛል።
21 ለማንም አላደላም፤ሰውንም አላቈላምጥም።