18 ባለጠግነት እንዳያታልልህ፣የእጅ መንሻ ብዛትም እንዳያስትህ ተጠንቀቅ።
19 ባለጠግነትህም ሆነ ብርቱ ጥረትህ ሁሉ፣ችግር ውስጥ እንዳትገባ ሊረዳህ ይችላልን?
20 ሰዎች ከቤታቸው የሚወሰዱበትን፣ሌሊት አትመኝ።
21 ከመከራ ይልቅ መርጠኸዋልና፣ወደ ክፋት እንዳትመለስ ተጠንቀቅ።
22 “እነሆ፤ እግዚአብሔር በኀይሉ ከፍ ከፍ ብሎአል፤እንደ እርሱስ ያለ አስተማሪ ማን ነው?
23 እርሱን መንገድ የሚመራው፣ወይም ‘ይህን አጥፍተሃል’ የሚለው ማን ነው?
24 ሰዎች በመዝሙር ያወደሱትን፣የእርሱን ሥራ ማወደስ አትዘንጋ።