1 ልቤ በዚህ በኀይል ይመታል፤ከስፍራውም ዘለል ዘለል ይላል።
2 ስሙ! የድምፁን ጩኸት ስሙ፤ከአፉ የሚወጣውን ጒርምርምታ አድምጡ።
3 መብረቁን ከሰማይ ሁሉ በታች ያባርቃል፤ወደ ምድርም ዳርቻ ይልካል።
4 ከዚያም በኋላ የድምፁ ጩኸት ይመጣል፤በድምፁም ግርማ ያንጐደጒዳል፤ድምጹ በተሰማ ጊዜ፣መብረቁን የሚከለክል የለም።
5 የእግዚአብሔር ድምፅ በሚያስደንቅ ሁኔታ ያንጐደጒዳል፤እኛ የማናስተውለውንም ታላቅ ነገር ያደርጋል።