21 ያን ጊዜ ተወልደሃል! ዕድሜህ ትልቅ ነውና፣አንተስ በእርግጥ ሳታውቅ አትቀርም!
22 “ወደ በረዶው መጋዘን ገብተሃልን?የዐመዳዩንስ ማከማቻ አይተሃልን?
23 ይኸውም ለመከራ ጊዜ፣ለጦርነትና ለውጊያ ቀን ያስቀመጥሁት ነው።
24 መብረቅ ወደሚሰራጭበት ቦታ የሚያደርሰው መንገድ፣የምሥራቅም ነፋስ በምድር ላይ ወደሚበተንበት ስፍራ የሚወስደው የትኛው ነው?
25 ለዝናብ መውረጃን፣ለመብረቅም መንገድን ያበጀ ማን ነው?
26 በዚህም ማንም የማይኖርበትን ምድር፣ሰውም የሌለበትን ምድረ በዳ የሚያጠጣ፣
27 ባድማውንና በረሓውን መሬት የሚያጠግብ፣ሣርም እንዲበቅልበት የሚያደርግ ማን ነው?