28 ዝናብ አባት አለውን?የጤዛን ጠብታ ማን ወለደው?
29 በረዶ ከማን ማሕፀን ይወጣል?የሰማዩንስ ዐመዳይ ማን ይወልዳል?
30 ውሆች እንደ ድንጋይ ይጠነክራሉ፤የጥልቁ ገጽ እንደ በረዶ ይጋገራል።
31 “ፕልያዲስ የተባሉትን ውብ ከዋክብት ልትለጒም፣ወይም የኦርዮንን ማሰሪያ ልትፈታ ትችላለህን?
32 ማዛሮት የተባለውን የክዋክብት ክምችት በወቅቱ ልታወጣ፣ወይም ድብ የተባለውን ኮከብና ልጆቹን ልትመራ ትችላለህ?
33 የሰማያትን ሥርዐት ታውቃለህ?ይህንስ በምድር ላይ እንዲሠለጥን ማድረግ ትችላለህ?
34 “ድምፅህን ወደ ደመናት አንሥተህ፣ራስህን በጐርፍ ማጥለቅለቅ ትችላለህን?