4 “ምድርን በመሠረትሁ ጊዜ አንተ የት ነበርህ?በእርግጥ የምታስተውል ከሆንህ፣ ንገረኝ።
5 ካወቅህ፣ መጠኗን ለይቶ ማን ወሰነ?በላይዋስ መለኪያ ገመድ የዘረጋ ማን ነው?
6 መሠረቶቿ ምን ላይ ተተከሉ?የማእዘን ድንጋይዋንስ ማን አቆመ?
7 ይህም የሆነው የንጋት ከዋክብት በዘመሩበት ጊዜ፣መላእክትም እልል ባሉበት ጊዜ ነበር።
8 “ባሕር ከማሕፀን በወጣ ጊዜ፣በር የዘጋበት ማን ነው?
9 ደመናውን ልብሱ፣ጨለማንም መጠቅለያው አደረግሁለት፣
10 ድንበር ወሰንሁለት፤መዝጊያና መወርወሪያውን አበጀሁለት።