16 በረዶ በሟሟ ጊዜ ወንዙ ይደፈርሳል፤ዐመዳይም በቀለጠ ጊዜ ይሞላል፤
17 በበጋ ወራት ግን ይጠፋል፤በሙቀትም ጊዜ መፋሰሻው ላይ አይገኝም።
18 ሲራራ ነጋዴዎች ውሃ አጥተው መንገዳቸውን ይቀይራሉ፤ወደ በረሓም ገብተው ይጠፋሉ።
19 የቴማን ነጋዴዎች ውሃ ይፈልጋሉየሳባ መንገደኞችም ተስፋ ያደርጋሉ፤
20 እርግጠኞች ሆነው ስለ ነበር ተሰቀቁ፤እዚያ ደረሱ፣ ግን ዐፈሩ።
21 አሁንም እናንተ እንደዚያ ሆናችሁብኝ፣መከራዬን አይታችሁ ፈራችሁ።
22 ለመሆኑ፣ ‘ስለ እኔ ሆናችሁ አንድ ነገር ስጡልኝ፣በዕዳ የተያዘብኝንም በሀብታችሁ አስለቅቁልኝ!’ ብያለሁን?