12 ገና በማደግ ላይ እያለ ሳይታጨድ፣ከሌሎች ዕፀዋት ፈጥኖ ይደርቃል።
13 እግዚአብሔርን የሚረሱ መጨረሻቸው እንዲህ ነው፤አምላክ የለሽ ኑሮ የሚኖሩም ሁሉ ተስፋቸው ትጠፋለች።
14 መተማመኛው ቀጭን ክር፣ድጋፉም የሸረሪት ድር ነው።
15 ድሩ ላይ ቢደገፍ፣ ይበጠስበታል፤አጥብቆም ቢይዘው አይጸናም።
16 ውሃ እንደ ጠገበ ተክል፣ ፀሓይ እየሞቀው፣ቅርንጫፉን ሁሉ በአትክልቱ ስፍራ ላይ ይዘረጋል።
17 ሥሩን በድንጋይ ክምር ላይ ይጠመጥማል፤በዐለትም መካከል ስፍራ ያበጃል።
18 ከስፍራው ሲወገድ ግን፣ያ ቦታ ‘አይቼህ አላውቅም’ ብሎ ይክደዋል።