16 ጠርቼው ‘አቤት!’ ቢለኝም፣ያዳምጠኛል ብዬ አላምንም።
17 በዐውሎ ነፋስ ይሰብረኛል፤ቍስሌንም ያለ ምክንያት ያበዛል፤
18 ምሬትን አጠገበኝ እንጂ፣ለመተንፈስ እንኳ ፋታ አልሰጠኝም።
19 የኀይል ነገር ከተነሣ፣ እርሱ ኀያል ነው!የፍትሕም ነገር ከተነሣ፣ መጥሪያ ሊሰጠው የሚችል ማን ነው?
20 ንጹሕ ብሆን እንኳ፣ አንደበቴ ይፈርድብኛል፣እንከን የለሽ እንኳ ብሆን፣ በደለኛ ያደርገኛል።
21 “ያለ ነቀፋ ብሆንም እንኳ፣ስለ ራሴ ግድ የለኝም፤የገዛ ሕይወቴንም እንቃታለሁ።
22 ሁሉም አንድ ነው፤‘እርሱ ጻድቁንና ኀጥኡን ያጠፋል’ የምለውም ለዚህ ነው።