1 እግዚአብሔር (ያህዌ) ሙሴን እንዲህ አለው፤
2 “ለእስራኤላውያን የምሰጠውን የከነዓንን ምድር እንዲሰልሉ ጥቂት ሰዎች ላክ፤ ከእያንዳንዱም የአባቶች ነገድ አለቃ ይላክ።”
3 ስለዚህ ሙሴ በእግዚአብሔር (ያህዌ) ትእዛዝ ከፋራን ምድረ በዳ እነዚህን ላካቸው፤ ሁሉም የእስራኤላውያን አለቆች ነበሩ፤
4 ስማቸውም እንደሚከተለው ነው፤ከሮቤል ነገድ፣ የዘኩር ልጅ ሳሙኤል፤