ዘኁልቍ 24 NASV

1 በለዓምም እግዚአብሔር (ያህዌ) እስራኤልን መባረክ እንደ ወደደ ባየ ጊዜ፣ እንደ ሌላው ጊዜ ሁሉ አስማት ለመሻት አልሄደም፤ ነገር ግን ፊቱን ወደ ምድረ በዳ መለሰ።

2 በለዓም አሻግሮ ተመልክቶ እስራኤል በየነገድ በየነገዱ ሆኖ መስፈሩን ሲያይ የእግዚአብሔር (ኤሎሂም) መንፈስ በላዩ መጣበት፤

3 ንግሩንም እንዲህ ሲል ጀመረ፤“የዚያ ዐይኑ የተከፈተለት፣የቢዖር ልጅ የበለዓም ንግር፣

4 የዚያ የአምላክን (ኤሎሂም) ቃል የሚሰማ፣ሁሉን የሚችል የአምላክን ራእይ የሚያይ፣ከመሬት የተደፋው ዐይኖቹም የተከፈቱለት ሰው ንግር፤

5 “ያዕቆብ ሆይ፤ ድንኳኖችህ፣እስራኤል ሆይ፤ ማደሪያዎችህ እንዴት ያማሩ ናቸው!

6 “እንደ ሸለቆዎች፣በወንዝ ዳር እንዳሉም የአትክልት ስፍራዎች ተዘርግተዋል፤ በእግዚአብሔር (ያህዌ) እንደ ተተከሉ ሬቶች፣በውሃም አጠገብ እንዳሉ ዝግባዎች ናቸው።

7 ከማድጋቸው ውሃ ይፈሳል፤ዘራቸውም የተትረፈረፈ ውሃ ያገኛል፤“ንጉሣቸው ከአጋግ ይልቃል፤መንግሥታቸውም ከፍ ከፍ ይላል፤

8 “እግዚአብሔር (ኤሎሂም) ከግብፅ አወጣቸው፤ብርታታቸውም እንደ ጎሽ ብርታት ነው፤ጠላቶች የሆኑአቸውን ሕዝብ ያነክታሉ፤ዐጥንቶቻቸውን ያደቅቃሉ፤በፍላጾቻቸው ይወጓቸዋል።

9 እንደ አንበሳ አድፍጠዋል፤እንደ እንስቲቱም አንበሳ አድብተዋል፤ ሊቀሰቅሳቸውስ የሚችል ማን ነው?“የሚባርኩህ ቡሩክ፣የሚረግሙህም ርጉም ይሁኑ።”

10 ከዚያም ባላቅ፣ በበለዓም ላይ እጅግ ተቈጣ፤ እጆቹንም አጨብጭቦ እንዲህ አለው፤ “ጠላቶቼን እንድትረግምልኝ ጠራሁህ፤ አንተ ግን ሦስቱንም ጊዜ ባረክሃቸው።

11 በል ቶሎ ወደ ቤትህ ሂድልኝ፤ ወሮታህን አሳምሬ ልከፍልህ ነበር፤ እግዚአብሔር (ያህዌ) ግን እንዳታገኝ ከለከለህ።”

12 በለዓምም ለባላቅ እንዲህ ሲል መለሰለት፤ ወደ እኔ ለላክሃቸው ሰዎች እንዲህ ብዬ ነግሬአቸው አልነበረምን?

13 ‘ሌላው ይቅርና ባላቅ በብርና በወርቅ የተሞላ ቤተ መንግሥቱን ቢሰጠኝ እንኳ፣ እግዚአብሔር (ያህዌ) የሚለውን ብቻ ከመናገር በስተቀር ከእግዚአብሔር (ያህዌ) ትእዛዝ ውጭ በራሴ ሐሳብ በጎም ሆነ ክፉ ማድረግ አልችልም።’

14 እንግዲህ ወደ ሕዝቤ እመለሳለሁ፤ ይሁን እንጂ በሚመጣው ዘመን ይህ ሕዝብ በሕዝብህ ላይ የሚያደርገውንና ልንገርህ።”

አራተኛው የበለዓም ንግር

15 ከዚያም እንዲህ ሲል ንግሩን ጀመረ፤“የቢዖር ልጅ የበለዓም ንግር፤የዚያ ዐይኑ የተከፈተለት ሰው ንግር።

16 የዚያ የአምላክን (ኤሎሂም) ቃል የሚሰማ፣ከልዑልም ዕውቀትን ያገኘው፣ሁሉን ከሚችለው ራእይ የሚገለጥለት፣መሬት የተደፋው፣ ዐይኖቹም የተገለጡለት ሰው ንግር፤

17 “አየዋለሁ፤ አሁን ግን አይደለም፤እመለከተዋለሁ፤ በቅርቡ ግን አይደለም፤ኮከብ ከያዕቆብ ይወጣል፤በትረ መንግሥት ከእስራኤል ይነሣል።የሞዓብን ግንባሮች፣የሤትንም ወንዶች ልጆች ራስ ቅል ያደቃል።

18 ኤዶም ይሸነፋል፤ጠላቱ ሴይርም ድል ይሆናል፤እስራኤል ግን እየበረታ ይሄዳል።

19 ገዥ ከያዕቆብ ይወጣል፤የተረፉትንም የከተማዪቱን ነዋሪዎች ይደመስሳል።”

የመጨረሻዎቹ የበለዓም ንግሮች

20 ከዚያም በለዓም አማሌቅን አይቶ ንግሩን እንዲህ ሲል ጀመረ፤“አማሌቅ ከሕዝቦች የመጀመሪያው ነበር፤በመጨረሻ ግን ይደመሰሳል።”

21 ቄናውያንንም አይቶ ንግሩን እንዲህ ሲል ጀመረ፤“መኖሪያህ አስተማማኝ ነው፤ጐጆህም በዐለት ውስጥ ተሠርቶአል፤

22 ያም ሆኖ ግን እናንት ቄናውያን፤አሶር በምርኮ ሲወስዳችሁ ትደመሰሳላችሁ።”

23 ከዚያም ንግሩን ቀጠለ፤“አቤት! አምላክ (ኤሎሂም) ይህንሲያደርግ ማን ይተርፋል?

24 መርከቦች ከኪቲም ዳርቻዎችይመጣሉ፤አሦርንና ዔቦርን ይይዛሉ፤እነርሱም ደግሞ ይደመሰሳሉ።

25 ከዚህ በኋላ በለዓም ተነሥቶ ወደ ቤቱ ተመለሰ፤ ባላቅም መንገዱን ቀጠለ።

ምዕራፎች

1 2 3 4 5 6 7 8 9 10 11 12 13 14 15 16 17 18 19 20 21 22 23 24 25 26 27 28 29 30 31 32 33 34 35 36