12 ከዳን ነገድ፣ የገማሊ ልጅ ዓሚኤል፤
13 ከአሴር ነገድ፣ የሚካኤል ልጅ ሰቱር፤
14 ከንፍታሌም ነገድ፣ የያቢ ልጅ ናቢ፤
15 ከጋድ ነገድ፣ የማኪ ልጅ ጉዲኤል።
16 እንግዲህ ምድሪቱን እንዲሰልሉ ሙሴ የላካቸው ሰዎች ስም ይህ ነው። ሙሴ ለነዌ ልጅ ለአውሴ፣ “ኢያሱ” የሚል ስም አወጣለት።
17 ሙሴም ከነዓንን እንዲሰልሉ በላካቸው ጊዜ እንዲህ አላቸው፤ “ነጌብን ዘልቃችሁ ወደ ተራራማው አገር ግቡ።
18 ምድሪቱ ምን እንደምትመስልና የሚኖሩባትም ሰዎች ብርቱዎች ወይም ደካሞች፣ ጥቂቶች ወይም ብዙዎች መሆናቸውን እዩ።