37 ከነዚህም ለእግዚአብሔር (ያህዌ) የተሰጠ ግብር ስድስት መቶ ሰባ አምስት ነበር።
38 ሠላሳ ስድስት ሺህ የቀንድ ከብት፣ ከነዚህም ለእግዚአብሔር (ያህዌ) የተሰጠው ግብር ሰባ ሁለት ነበር።
39 ሠላሳ ሺህ አምስት መቶ አህያ፣ ከነዚህም ለእግዚአብሔር (ያህዌ) የተሰጠው ግብር ሥልሳ አንድ ነበር።
40 ዐሥራ ስድስት ሺህ ሰው፤ ከነዚህም ለእግዚአብሔር (ያህዌ) የተሰጠው ግብር ሠላሳ ሁለት ነበር።
41 ሙሴም እግዚአብሔር (ያህዌ) እንዳዘዘው የእግዚአብሔር (ያህዌ) ድርሻ የሆነውን ግብር ለአልዓዛር ሰጠው።
42 ሙሴ ከዘመቱት ሰዎች የለየው የእስራኤላውያን እኩሌታ ድርሻ ማለትም፣
43 የማኅበረ ሰቡ ድርሻ ይህ ነበር፤ ሦስት መቶ ሠላሳ ሰባት ሺህ አምስት መቶ በግ፣