39 የምናሴ ልጅ የሆነው የማኪር ዘሮች ወደ ገለዓድ ሄደው ምድሪቱን በመያዝ፣ እዚያ የነበሩትን አሞራውያን አሳደዱአቸው፤
40 ስለዚህ ሙሴ ገለዓድን የምናሴ ዘሮች ለሆኑት ለማኪራውያን ሰጣቸው፤ እነርሱም መኖሪያቸውን በዚያው አደረጉ።
41 ከምናሴ ነገድ የሆነው ኢያዕር መኖሪያቸውን ወስዶ፣ “የኢያዕር መንደሮች” ብሎ ሰየማቸው።
42 እንዲሁም ኖባህ ቄናትንና በዙሪያዋ ያሉትን መንደሮች በመያዝ በራሱ ስም፣ “ኖባህ” ብሎ ጠራቸው።