21 ከዚያም የእስራኤል ሕዝብ ከሁለት ተከፈለ፣ ይህም ግማሹ የጎናትን ልጅ ታምኒን ለማንገሥ ሲሆን፣ የቀረው ደግሞ ዖምሪን በመደገፍ ነበር።
22 ሆኖም የዖምሪ ተከታዮች ከጎናት ልጅ ከታምኒ ተከታዮች ይልቅ በረቱ፤ ስለዚህ ታምኒ ሞተ፤ ዖምሪም ነገሠ።
23 የይሁዳ ንጉሥ አሳ በነገሠ በሠላሳ አንደኛው ዓመት፣ ዖምሪ በእስራኤል ላይ ነገሠ፤ ዐሥራ ሁለት ዓመትም ገዛ፤ ከዚህም ውስጥ ስድስቱን ዓመት የገዛው በቴርሳ ሆኖ ነው።
24 እርሱም የሰማርያን ኰረብታ በሁለት መክሊት ጥሬ ብር ከሳምር ላይ ገዝቶ ከተማ ሠራባት፤ ስሟንም በቀድሞው የተራራዋ ባለቤት በሳምር ስም ሰማርያ ብሎ ጠራት።
25 ይሁን እንጂ ዖምሪ በእግዚአብሔር ፊት ክፉ ድርጊት ፈጸመ፤ ከእርሱ አስቀድሞ ከነበሩትም ይልቅ የበለጠ ኀጢአት ሠራ።
26 እርሱም እስራኤል በማይረቡ ጣዖቶቻቸው፣ የእስራኤልን አምላክ እግዚአብሔርን ለቊጣ እንዲያነሣሡት ባደረገው በናባጥ ልጅ በኢዮርብዓም መንገድ ሁሉና እርሱም ኀጢአት ሠርቶ እስራኤልም እንዲሠሩ ባደረገው ኀጢአት ተመላለሰ።
27 ሌላው ዖምሪ በዘመኑ የፈጸመው፣ ያደረገውና ያከናወነው ሁሉ በእስራኤል የነገሥታት ታሪክ ተጽፎ የሚገኝ አይደለምን?