2 እነርሱም፣ “እነዚህን ነገሮች የምታደርገው በምን ሥልጣን እንደሆነ ንገረን፤ ሥልጣንስ የሰጠህ ለመሆኑ እርሱ ማን ነው?” ብለው ጠየቁት።
3 እርሱም እንዲህ ሲል መለሰላቸው፤ “እኔም አንድ ጥያቄ ልጠይቃችሁ፤ እስቲ መልሱልኝ፤
4 የዮሐንስ ጥምቀት ከሰማይ ነበር ወይስ ከሰው?”
5 እነርሱም እንዲህ ብለው እርስ በርስ ተመካከሩ፤ “ ‘ከሰማይ’ ብንል፣ ‘ታዲያ፣ ለምን አላመናችሁበትም?’ ይለናል፤
6 ‘ከሰው’ ብንል ሕዝቡ ሁሉ ዮሐንስ ነቢይ መሆኑን ስለ ሚያምኑ በድንጋይ ይወግሩናል።”
7 ስለዚህ፣ “ከየት እንደሆነ አናውቅም” ብለው መለሱለት።
8 ኢየሱስም፣ “እንግዲያውስ እኔም እነዚህን ነገሮች በምን ሥልጣን እንደማደርግ አልነግራችሁም” አላቸው።