1 ነገሥት 5:9-15 NASV

9 ሰዎቼ ግንዱን ከሊባኖስ እስከ ባሕሩ ድረስ ጐትተው ያወርዳሉ፤ እኔም ግንዱ ሁሉ ታስሮ አንተ እስከ ወሰንኸው ስፍራ በባሕር ተንሳፎ እንዲደርስ አደርጋለሁ፤ እዚያም እኔ እፈታዋለሁ፣ አንተም ትወስደዋለህ፤ አንተም ለቤተ ሰቤ ቀለብ በመስጠት ፍላጎቴን ታሟላለህ።”

10 በዚህ ሁኔታ ኪራም ለሰሎሞን የሚያስፈልገውን የዝግባና የጥድ ግንድ በሙሉ ያቀርብለት ጀመር፤

11 ሰሎሞን ደግሞ ለኪራም ቤተ ሰው ቀለብ እንዲሆን ሃያ ሺህ የቆሮስ መስፈሪያ ስንዴ፣ ሃያ ሺህ ኮር ንጹሕ የወይራ ዘይት ሰጠው፤ ይህን ባለማቋረጥ በያመቱ ለኪራም ይሰጥ ነበር።

12 እግዚአብሔርም በገባለት ተስፋ መሠረት ለሰሎሞን ጥበብን ሰጠው፤ በኪራምና በሰሎሞን መካከልም መልካም ግንኙነት ነበር፤ ሁለቱም ቃል ኪዳን አደረጉ።

13 ንጉሥ ሰሎሞን ከመላው እስራኤል የጒልበት ሠራተኞችን መለመለ፤ ቍጥራቸውም ሠላሳ ሺህ ነበር።

14 እነዚህንም አንድ ወር በሊባኖስ እንዲሠሩ፣ ሁለት ወር በቤታቸው እንዲያርፉ በማድረግ፣ ዐሥር ዐሥር ሺዉን ወር ተራ አግብቶ ላካቸው። የጒልበት ሠራተኞቹም አለቃ አዶኒራም ነበር።

15 ሰሎሞንም በኰረብታማው አገር ሰባ ሺህ ተሸካሚዎችና ሰማንያ ሺህ ድንጋይ ጠራቢዎች ነበሩት፤