1 በዚያን ዕለት ዲቦራና የአቢኒኤም ልጅ ባርቅ ይህን ቅኔ ተቀኙ፤
2 “በእስራኤል ያሉ መሳፍንት ሲመሩ፣ሕዝቡም በፈቃዱ ራሱን ሲያስገዛ፣ እግዚአብሔርን አመስግኑ።
3 “እናንት ነገሥታት ይህን ስሙ፤ገዦችም አድምጡ፤ ለእግዚአብሔር እዘምራለሁ፤ ደግሜምለእስራኤል አምላክ ለእግዚአብሔር እቀኛለሁ።
4 “እግዚአብሔር ሆይ፤ ከሴይር በወጣህ ጊዜ፣ከኤዶም ምድርም በተነሣህ ጊዜ፣ምድር ተንቀጠቀጠች፤ ሰማያትም ዝናብ አዘነቡ፤ደመናዎችም ውሃ አፈሰሱ።