1 በዚያን ዕለት ዲቦራና የአቢኒኤም ልጅ ባርቅ ይህን ቅኔ ተቀኙ፤
2 “በእስራኤል ያሉ መሳፍንት ሲመሩ፣ሕዝቡም በፈቃዱ ራሱን ሲያስገዛ፣ እግዚአብሔርን አመስግኑ።
3 “እናንት ነገሥታት ይህን ስሙ፤ገዦችም አድምጡ፤ ለእግዚአብሔር እዘምራለሁ፤ ደግሜምለእስራኤል አምላክ ለእግዚአብሔር እቀኛለሁ።
4 “እግዚአብሔር ሆይ፤ ከሴይር በወጣህ ጊዜ፣ከኤዶም ምድርም በተነሣህ ጊዜ፣ምድር ተንቀጠቀጠች፤ ሰማያትም ዝናብ አዘነቡ፤ደመናዎችም ውሃ አፈሰሱ።
5 ተራሮች በሲና አምላክ በእግዚአብሔር ፊት፣በእስራኤልም አምላክ በእግዚአብሔር ፊት ተናወጡ።
6 “በዓናት ልጅ በሰሜጋር ዘመን፣በኢያዔል ጊዜ መንገዶች ባድማ ሆኑ፤ተጓዦችም በጠመዝማዛ መንገድ ሄዱ።
7 ለእስራኤል እናት ሆኜእኔ ዲቦራ እስክነሣ ድረስበእስራኤል ያለው የከተማ ኑሮ አበቃለት፤