3 “እናንት ነገሥታት ይህን ስሙ፤ገዦችም አድምጡ፤ ለእግዚአብሔር እዘምራለሁ፤ ደግሜምለእስራኤል አምላክ ለእግዚአብሔር እቀኛለሁ።
4 “እግዚአብሔር ሆይ፤ ከሴይር በወጣህ ጊዜ፣ከኤዶም ምድርም በተነሣህ ጊዜ፣ምድር ተንቀጠቀጠች፤ ሰማያትም ዝናብ አዘነቡ፤ደመናዎችም ውሃ አፈሰሱ።
5 ተራሮች በሲና አምላክ በእግዚአብሔር ፊት፣በእስራኤልም አምላክ በእግዚአብሔር ፊት ተናወጡ።
6 “በዓናት ልጅ በሰሜጋር ዘመን፣በኢያዔል ጊዜ መንገዶች ባድማ ሆኑ፤ተጓዦችም በጠመዝማዛ መንገድ ሄዱ።
7 ለእስራኤል እናት ሆኜእኔ ዲቦራ እስክነሣ ድረስበእስራኤል ያለው የከተማ ኑሮ አበቃለት፤
8 አዳዲስ አማልክትን በተከተሉ ጊዜ፣ጦርነት እስከ ከተማው በር መጣ፤ጋሻም ሆነ ጦር፣በአርባ ሺህ እስራኤላውያን መካከል አልተገኘም።
9 ልቤ ከእስራኤል መሳፍንት፣ፈቃደኞችም ከሆኑ ሰዎች ጋር ነው፤እግዚአብሔር ይመስገን።